Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርት​ የዋሊያዎቹ የቻን ቆይታና ቀጣይ ዝግጅት

​ የዋሊያዎቹ የቻን ቆይታና ቀጣይ ዝግጅት

ቀን:

በአራተኛው የቻን ውድድር ጉዞ በምድብ ለ ከካሜሩን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም አንጎላ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ ጨዋታ 3ለ0 በመሸነፍ፣ እንዲሁም በሁለተኛው ጨዋታ ከካሜሩን ጋር ባደረገው ጨዋታ 0ለ0 በመለያየት እንዲሁም በመጨረሻ ጨዋታ በአንጎላ ብሔራዊ ቡድን 2ለ1 በሆነ ውጤት በመረታት አንድ ነጥብ ብቻ ይዞ ከውድድር ውጪ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተለይ ዋሊያዎቹ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከተደረገው የሴካፋ ውድድር በኋላ ወደ ቻን ያመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከካሜሩን አቻው ጋር ካደረገው ጨዋታ ውጪ ጥሩ የሚባል ጉዞ እንዳላሳለፈ ውጤቱ አመላካች ነው፡፡

በተለይ የመጨረሻው የምድብ ጨዋታቸውን ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ከአንጎላ አቻቸው ጋር ያደረጉት ዋሊያዎቹ ቀደም ብለው ከካሜሩን አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በማሰብ፣ ከምድብ ለ አንጎላ በሁለት ጨዋታ ዝቅተኛ ውጤት ያመጣች አገር በመሆንዋ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ግምት ያልሰጠ አልነበረም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሩዋንዳ ሲያመራ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የምድቡን መጨረሻ ጨዋታ እስከሚያደርግበት ቀን ድረስ ብቻ የመጓጓዣ ትኬት መቁረጡ ብዙዎቹን ያነጋገረ ጉዳይ ቢሆንም፣ የቡድን መሪው አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ‹‹ውጤቱን ከመገመት አኳያ አይደለም›› በማለት ሩዋንዳ ለሚገኙት ጋዜጠኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ የደጋፊን ቀልብ የሚስብና የውጤት ረሃብን የሚያስታግስ የተሟላ ብሔራዊ ቡድን ለመመሥረት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገር ውስጥ ሊጎችን በማቆም ጭምር ውድድሮች ቢደረጉም፣ እስካሁን በተደረጉት የማጣሪያ ጨዋታዎችና ከፍተኛ ውድድሮች ላይ ዋሊያዎቹ የሚያሳዩት እንቅስቃሴ የሚያስደስት እንዳልሆነ የተለያዩ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተለይ ለ2016 የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከቀረቡት አገሮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግምት ካገኙ ቡድኖች ውስጥ ቀዳሚ መሆናቸውን በተለያዩ ሚዲያዎች በሰፊው ተዘግቧል፡፡ በውድድሩ ላይ የተገኙ የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የስፖርት ባለሙያዎች ለአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ስብስብ የነበራቸውን ከፍተኛ ግምት ዋሊያዎቹ ያደረጉት ጨዋታ ላይ ማየት እንዳልቻሉ እንደ ሱፐር ስፖርት የመሳሰሉ ሚዲያዎች በዜናዎቻቸው አስፍረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመደበበት ምድብ ለ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢትዮጵያን በመረታት ቀዳሚ ሲሆን፣ ካሜሩን አንጎላን 1ለ0 በመርታት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ቆይቷል፡፡ በመጨረሻው ጨዋታ ካሜሩን ከምድቡ ሰባት ነጥብ በመያዝ አንደኛ ሆኖ ወደ ሩብ ፍጻሜው ሲቀላቀል፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በስድስት ነጥብ ሁለተኛ በመሆን  ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡

የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን ሦስት ነጥብ ሦስተኛ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንድ ነጥብ በመያዝ ከምድቡ አራተኛ ሆኖ ወደ አገር ቤት ተሰናባች ሆኗል፡፡

በምድብ ሀ አዘጋጅዋ ሩዋንዳና አይቨሪኮስት በእኩል ስድስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተለያይተው ከምድባቸው ሲያልፉ፣ ሞሮኮና ጋቦን ተሰናባች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከምድብ ሀናለ በቀጥታ ያለፉት አገሮች ሩዋንዳና ዴሞክራቲክ ኮንጎ በኪጋሊ ስታዲየም ጥር 21 የሩብ ፍጻሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፣ ካሜሩን ከአይቨሪኮስት በተመሳሳይ ስታዲየም ጥር 22 ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡ ከውድድሩ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የተመለሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በቂ የዝግጅት ጊዜ አለመኖር ለውጤቱ መጥፋት መንስኤ ነው በማለት ለሚዲያዎች ተናግረዋል፡፡

ዋሊያዎቹ በቻን በነበራቸው ቆይታ መጋቢት ወር ላይ ለሚጠብቃቸው የ2017 ጋቦን አፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ልምድ እንደተገኘ አሠልጣኙ ገልጸዋል፡፡ ዋሊያዎቹ ለዘንድሮ የቻን ጉዞዋቸው ከምድባቸው አንድ ነጥብና በሥዩም ተስፋዬ አማካይነት አንድ ግብ ማስመዝገባቸው እንደ ታሪክ ቢጻፍም፣ መጋቢት ላይ ከአልጄሪያ አቻቸው የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህርዳር ስታዲየም የሌሴቶ አቻውን 2ለ1 በማሸነፍ፣ እንዲሁም ከሲሼልስ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1ለ1 በመውጣት 4 ነጥብ በመያዝ ከምድቡ አልጄሪያን በመከተል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ለቀጣይ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለመዘጋጀት ከወዲሁ ዝግጅቱን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ምድባቸውን በአንድ ነጥብና በአራት የግብ ዕዳ ይዘው ያጠናቀቁት ዋሊያዎቹ በተካፋይነታቸው ያገኙትን 100 ሺሕ ዶላር ይዘው ከሩዋንዳ ጥር 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...