Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍርፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

ቀን:

‹‹ሌኒንና እሱ የመሠረተው መንግሥት በጭካኔ የሩሲያን የመጨረሻ ንጉሥና ቤተሰቦቹን በመፍጀት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቀሳውስትን በመግደልና የሩሲያ ግዛትን አስተዳደራዊ ድንበሮች ዘርን መሥፈርት ባደረገ መንገድ በማካለል ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ ቀብረዋል፡፡››

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሰኞ ጥር 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በሞስኮ ደቡባዊ ከተማ ስታቭሮፖል ከደጋፊዎቻቸው ጋር ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት መሥራችና የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሌኒንና በቮልሼቪክ መንግሥት፣ በአገሪቱ ጭካኔ የተሞላባቸው ጭቆናዎች ተፈጽመዋል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኮሙዩኒስት ሩሲያ መሪዎች ላይ ቁጥብ የነበሩት ፑቲን፣ በነሌኒን የተፈጸመው ስህተት ለአሁኑ የዩክሬን ቀውስ ምክንያት ሆኗል በማለት ክራይሚያን ከዩሬን ፈልቅቀው መውሰዳቸውን ትክክለኛነት ተናግረዋል፡፡ በተለይ የሌኒን የፌዴራል ጽንሰ ሐሳብ እስከ መገንጠል የሚለው የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት እ.ኤ.አ. በ1991 እንድትበታተን አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉም ይተቻሉ፡፡ ፑቲን ከዚህ ቀደም የስታሊንን ግድያዎችና አስከፊ ተግባራት ወቅሰው፣ ናዚን ማሸነፉን ግን በበጎ አስታውሰዋል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት ቭላድሚር ፑቲን ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...