Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊውጤታማ ወጣቶችን የሚሸልምና እውቅና የሚሰጥ ፕሮግራም ተጀመረ

ውጤታማ ወጣቶችን የሚሸልምና እውቅና የሚሰጥ ፕሮግራም ተጀመረ

ቀን:

‹‹ኢትዮጵያን ዩዝ አዋርድ›› የተባለና በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ የሆኑ ወጣቶችን የሚሸልምና እውቅና የሚሰጥ ዓመታዊ ፕሮግራም በብስራት ኤፍኤም ሬዲዮ 101.1 ኦያያ መልቲ ሚዲያና ኢኢጂ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ትብብር ተጀመረ፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጆች ጥር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ ያለው አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ወጣት እንደመሆኑ ያለውን እምቅ ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል ወጣቶች በሙያቸው የሚመዘኑባቸውን የተለያዩ ውድድሮች በማዘጋጀትና በመሸለም ለውጥ መፍጠር እንደሚቻል ፕሮጀክቱ ያምናል፡፡ በመሆኑም ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ የሚዘጋጀው ኢትዮጵያን ዩዝ አዋርድ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግር ፈቺ ምርምር በማድረግና በተግባር ላይ በማዋል ተጨባጭ ሥራ የሠሩ፣ በማኅበራዊና ሳይንስ ዘርፍ ፋይዳ ያለው ጥናትና ምርምር በማካሄድ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ፣ አገራዊ ፋይዳቸው የጐላና ለዜጐች በተለያዩ የሥራ ፈጠራ፣ በንግድ፣ በልማትና በኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት የላቀ ስኬት የተቀዳጁ፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በሆቴልና መዝናኛ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአስመጪና ላኪ ዘርፎች ተሰማርተው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ወጣቶችን፣ እንዲሁም በኪነ ጥበብ በሥነ ጽሑፍ፣ በጋዜጠኝነት፣ በመምህርነት፣ በበጐ አድራጊነት፣ በአገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ድርጅቶች አመራርነት ረገድ አርአያ የሚሆኑ ወጣቶችን አወዳድሮ ለመሸለም ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ደመቀ እንደሚሉት፣ በአሥራ ስድስቱ ዘርፎች አንደኛ የሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብና የዋንጫ ሽልማት ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ወጣቶች በሚገኙባቸው የተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች የማነቃቂያ ንግግር እንዲያደርጉ፣ ተሞክሯቸውም በተለያዩ መንገዶች ለሕዝቡ እንዲደርሱ ይደረጋል፡፡

ተወዳዳሪዎችም በመገናኛ ብዙኃን፣ ይፋ በሚደረጉ የስልክ ቁጥሮች፣ የኢሜይል፣ የፌስቡክ ገጽ፣ ኤስኤምኤስ አድራሻ እንዲሁም ዝግጀቱን በሚያስተባብረው ድርጅት ቢሮ አድራሻ በመጠቀም አቅሙ ያላቸውን መጠቆምና በግል በመወዳደር ተሳትፎ እንዲያደርጉ አዘጋጆቹ ጠይቀዋል፡፡

‹‹የወጣትነት ስኬትን እውቅና በመስጠት ወጣቶች እምቅ አቅማቸውን ይበልጥ ሥራ ላይ እንዲያውሉት በጊዜ ማበረታታቱ ለሌሎችም መነሳሳትን ለእነሱም ብርታትን ይሰጣል፡፡ በዋናነት ደግሞ ለአገር ልማት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፤›› ያሉት አቶ ስንታየሁ፣ ጥቆማው ከጥር 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጀምሮ በቀጣዮቹ በ15 ቀናት እንደሚጠናቀቅ፣ የተወዳዳሪዎች ውጤትም በሁለት ወራት ተጠናቅቆ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...