Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር የኤዩን ሽልማት አገኙ

ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር የኤዩን ሽልማት አገኙ

ቀን:

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የክዋሜ ኑክርማ ሽልማት ለሁለት አፍሪካውያን ሳይንቲስቶች ተበርክቷል፡፡ ምሥራቅ አፍሪካን በመወከል የተሸለሙት ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር ያለምፀሐይ መኰንን አንዷ ሲሆኑ፣ ባገኙት ስኬትና ለአኅጉሪቱ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ተመርጠዋል፡፡ ደቡባዊ አፍሪካን ወክለው የተሸለሙት ደግሞ ፕሮፌሰር መርዙክ ሀፊዳ ናቸው፡፡

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፣ ለፕሮፌሰር ያለምፀሐይ ሽልማቱ የተበረከተላቸው ለአኅጉሪቷ ዕድገት ከፍተኛ ሚና በተጫወተው ሳይንሳዊ ግኝታቸው ነው፡፡ ስምንተኛው የአፍሪካ ኅብረት የጀንደር ፕሪ ሰሚት በተጠናቀቀበት ወቅት ያገኙት ሽልማት በተለይም ሴት ሳይንቲስቶችን ታሳቢ በማድረግ መሰጠት ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

ሁለቱ ፕሮፌሰሮች የ20,000 ዶላር ሽልማት፣ የወርቅ ሜዳሊያና አበርክቷቸውን የሚገልጽ ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ፕሮፌሰር ያለምፀሐይ እ.ኤ.አ. በ1972 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በባዮሎጂ ትምህርት አግኝተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በትምህርት ክፍሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመውን የዙኦሎጂ ድኅረ ምረቃ ትምህርት ክፍል ከተቀላቀሉና ከመጀመሪያ ዙር ምሩቃን መካከል አንዷ ከመሆናቸውም በላይ በትምህርት ክፍሉ እንዲሁም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የዙኦሎጂ ምሩቅ ሆነዋል፡፡

ፒኤችዲያቸውን በሒውማን ፊዚዎሎጂ፣ ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሔድልበርግ ጀርመኒ በ1992 ያገኙ ሲሆን፣ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት በ2009 ነው፡፡ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪም በርካታ ሽልማቶችም ተበርክተውላቸዋል፡፡

የፕሮፌሰሯ ምርምሮች በዋነኛነት የሚያተኩሩት ማኅበረሰቡ በሚገለገልባቸውና መድኃኒትነት ባላቸው ዕፀዋት ላይ ነው፡፡ በቤተ ሙከራ ውስጥ ዕፅዋቱ ስላላቸው ጠቀሜታ ይመራመራሉ፡፡ በኢንዱስትሪዎች ተረፈ ምርትና በግብር ወቅት በሚለቀቁ ኬሚካሎች ሳቢያ በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጉዳቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥናቶችም ያደርጋሉ፡፡

ፕሮፌሰሯ ከአገር ውስጥና ከውጭ ተመራማሪዎች ጋር በጥምረት የሠሯቸው ጥናቶችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በ92 ሳይንሳዊ ጆርናሎች ላይ የሥራዎቻቸው ውጤቶች ታትመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ውስጥ በማስተማርና በመመራመር ላይ ይገኛሉ፡፡

በአመራርና በአባልነት የሚሳተፉባቸው የሙያ ማኅበራት ብዙ ናቸው፡፡ የኒዮርክ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ አባልም ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አባልና የኢትዮጵያን ውሜን ኢን ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ ዋና የቦርድ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም ሽልማት ካበረከቱላቸው ተቋሞች መካከል የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያን አግሪካልቸራል ሪሰርች ኦርጋናይዜሽን፣ ብሪትሽ ካውንስልና ሰርድ ወርልድ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በሽልማቱ ላይ የአፍሪካ ኅብረት የሳይንስና ቴክኖሎጂና ሒዩማን ሪሶርስስ ኮሚሽነር ዶ/ር ማርሻል ዲፓል ኦካንጋ፣ ሽልማቱ ለአፍሪካ ዕድገት ቁልፍ ሚና ያላቸው አበርክቶዎች የሚበረታቱበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በአፍሪካውያን ዘንድ በስፋት እንዲሰርጽ፣ ተመራማሪዎቹ እንዲታወቁና ዘርፉ ለአፍሪካ ዕድገት ያለው አስተዋጽኦ ቦታ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሽልማቱ በሪጅናል ደረጃ ለወጣት ተመራማሪዎች፣ ለወጣት ሴት ተመራማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፣ የአኅጉራዊው ዘርፍ ሽልማት ትልቅ ሥፍራ ይሰጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...