አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 1 ኪሎ ግራም የታላቅ ወይም የሽንጥ ስጋ
- 4 መካከለኛ ጭልፋ (600 ኪሎ ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
- 2 የሾርባ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
- 1 የሾርባ ማንኪያ መከለሻ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
- 4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- 3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
- ምጥን ሽንኩርት መጨመርና ማቁላላት፤
- ዘይት መጨመር፤
- አዋዜውንና ጥቁር ቅመሙን ጨምሮ በደንብ እንዲንተከተክ መተው፤
- ስጋውን አገንፍሎ ደቀቅ አድርጎ መክተፍና ውሃው መጠጥ ሲል መጨመር፤
- ውሃው ደረቅ ሲል ትንሽ ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማሸት፤
- በወፍራሙ እያንተከተኩ ማብሰልና ጨው መጨመር፤
- ርጥብ ቅመምና ቅቤ ጨምሮ በወፍራሙ ማንተክተክ፤
- በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመምና መከለሻውን አስተካከሎ ወፍራም መረቅ እንዲኖረው በማድረግ አንሰክስኮ ማውጣት፡፡
ደብረወርቅ አባተ (ሱሼፍ) ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)