ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል በሰሜን አሜሪካ ከሚያከናውናቸው ጥባበዊና ባህላዊ ተግባራት ባሻገር፣ በአዲስ አበባ የማዕከሉን ዓይነት መሰናዶ ለማቅረብ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተንቀሳቀሱ ባሉ በጎ ፈቃደኞች ኪናዊና ባህላዊ መድረኮች ሲዘጋጁ ቆይተዋል፡፡ ይህንኑ እንቅስቃሴ የሚያስቀጥል መሰናዶ ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ከ11 ሰዓት ጀምሮ በአክሱም ሆቴል ልዩ የኪነ ጥበብ መድረክ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባው አስተባባሪ ገልጿል፡፡ እንደ አስተባባሪው ይታገሱ ጌትነት ጦማር በዝግጅቱ ግጥም፣ ወግ፣ ግለ ወግ፣ የሐሳብ ቅብብሎሽና ሌሎች ዝግጅቶች በከያንያን ይቀርባሉ፡፡