የኢትዮጵያ ወጣቶች ሳይንስ አካዴሚ የመጀመሪያው የሆነውን በቀዶ ሕክምና ታሪክ ላይ የተመሠረተውን የሳይንስ ወግ ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በ11 ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ) በሚገኘው አዳራሽ ያቀርባል፡፡ ሳይንሳዊ ወግ አቅራቢው ዶ/ር አበበ በቀለ ሲሆኑ ውይይትም ይካሄዳል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት የሳይንስ ተመራማሪዎችን በማቀፍ የሚንቀሳቀሰው አካዴሚው ሊሠራቸው ካቀዳቸው ተግባራት ውስጥ አንዱ በየሁለት ወሩ የሳይንስ ወጎች (EtYAS Chats) በሚል መጠርያ ሳይንሳዊ ውይይት ማካሄድ ነው፡፡