‹‹ዓለም በጌታቸው ዐይን›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከፍቷል፡፡ ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ዐውደ ርዕይ አስመልክቶ ግንቦት 19 ቀን በ8 ሰዓት በጋለሪው ‹‹ጉዞ ታሪክ ምስል›› በሚል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነጥበብ ታሪክ ምሁራን በሚያቀርቡት ዳሰሳ ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ በዐውደ ርዕዩ መዝጊያም (ግንቦት 25) ‹‹ጉዞ ምስል ሙዚቃ›› እና ‹‹ፎቶ እንደ ጥበብ›› የሚል የውይይት መርሐ ግብር መዘጋጀቱን ኢጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡