Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ለግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ፈተና ሆነዋል

የአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ለግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ፈተና ሆነዋል

ቀን:

ከጥቂት ዓመት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየተገነቡ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሕንፃዎቹ ራሱን ችሎ ፈቃድ የሚሰጥበትም ሆነ የሚቆጣጠርበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሰ ተመለከተ፡፡

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ 26 ሺሕ ሕንፃዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን፣ በዚህ ዓመት በማዕከል ደረጃ ለ500 ፕሮጀክቶች የግንባታ ፈቃድ መሰጠቱ ታውቋል፡፡ በተለይ በባንኮችና በኢንሹራንስ ተቋማት ተመራጭ በሆነው ሠንጋ ተራና ዙርያው ከፍታቸው ከ36 እስከ 52 ፎቅ የሆኑ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየተገነቡ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚካሄዱ ግንባታዎች በጠቅላላ የግንባታ ፈቃድ የመስጠት፣ ግንባታቸውን የመቆጣጠርና ግንባታ ሲጠናቀቅም የመጠቀሚያ ፈቃድ የመስጠትም ሆነ የመንሳት ሥልጣን የተሰጠው ለአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ባንኮችና ኢንሹራንስ ተቋማት የሚገነቧቸው ፕሮጀክቶች ረዣዥምና ውስብስብ ባህሪ ያላቸው በመሆናቸው፣ እነዚህን ለማስተዳደር ባለሥልጣኑ ራሱን በሰው ኃይል ባለመደራጀቱ ሌሎች አማራጮችን ለማየት ተገዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ አለቃ ለሪፖርተተር እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ የሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ዲዛይን ሲቀርብለት ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር፣ ከአማካሪ ድርጅቶችና ከመሳሰሉ ድርጅቶች ቡድን በማቋቋም በጋራ ይመረመራል፡፡

‹‹ባለሥልጣኑ ራሱን ብቃት ባለው የሰው ኃይል እስኪያደራጅ ድረስ ሦስት መንገዶችን እናያለን፡፡ በወረዳ ደረጃ ለሚካሄዱ አነስተኛ ግንባታዎች ባለሙያዎች፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበር በማደራጀት፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ ደግሞ በአንድ ክፍለ ከተማ ናሙና ፕሮጀክት በመክፈት ጨረታ አውጥተን አርክቴክት መርጠን፣ እስከ አሥር ፎቅ ድረስ ያሉ ግንባታዎችን ዲዛይን እንዲመለከት እናደርጋለን፡፡ በማዕከል ደረጃ ራሳችንን እስክናደራጅ ድረስ በጋራ ዳኝነት እንሰጣለን፤›› በማለት አቶ መለሰ ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት፣ እስካሁን እየተገነቡ ካሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚገነባው ትልቁና ውስብስቡ ሕንፃ ነው፡፡ የሕንፃው ዲዛይንና ግንባታ በአንድ የቻይና ኩባንያ እየተካሄደ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አማካሪ ሆኖ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

በአብዛኛው ሕንፃዎቹ የሚገነቡት በውጭ ኮንትራክተር ሲሆን፣ የሚጠቀሙበት ቴክኖሎጂም እንዲሁ አዲስ ነው፡፡ የግንባታው ሒደትም በከተማው ባልተለመደ ሁኔታ ፈጣን ነው፡፡

እነዚህ አዳዲስ ክስተቶች ለከተማው አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ፈታኝ ሲሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ራሱን በዚሁ ደረጃ ለማደራጀት እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱ ተገልጿል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...