Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበደቡብ ክልል በመሬት መንሸራተት የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ክልል በመሬት መንሸራተት የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ቀን:

የፌዴራል መንግሥት ለተፈናቃዮች ዕርዳታ መላክ ጀመረ

በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ሁለት ዞኖች በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ መሬት በመንሸራተቱ የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የክልሉ መንግሥት ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከማምሻው ጀምሮ ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎችን መላክ ጀምሯል፡፡

ከዓርብ ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በደቡብ ክልል ከፍተኛ ዝናብ መጣል የጀመረ ሲሆን፣ በዚሁ ምክንያት የሲዳማ ዞን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ጋር በሚዋሰንበት ጭሬ ወረዳ 23 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በጋሞጎፋ ዞን ደረመሎ ወረዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከሁለቱም አካባቢዎች ለጊዜው ቁጥራቸው ያልተገለጸ ዜጎች ከመፈናቀላቸውም በላይ፣ 20 የሚጠጉ ዜጎች አካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡  

የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአካባቢዎቹ ከባድ ዝናብ በመጣሉና ተዳፋቶች በመሆናቸው የሰው ሕይወት አልፏል፡፡

‹‹የክረምቱ ወራት ጠንከር ያለ ዝናብ ሊኖረው የሚችል በመሆኑ፣ ከተዳፋቶቹ ቦታዎች ዜጎች ተነስተው በዘላቂነት መስፈር አለባቸው፤›› ሲሉ አቶ ምትኩ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

አቶ ምትኩ እንዳሉት ወረዳዎቹ፣ ዞኖቹና ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥትም በተጠየቀው መሠረት አስፈላጊውን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ወደ ሥፍራው እንዲጓዙ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ተመሳሳይ አደጋዎች እያጋጠሙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ አደጋ ሊያጋጥም ስለሚችል ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንና ዜጎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቶ ምትኩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...