Friday, January 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢዴፓ ፕሬዚዳንት የፓርቲውን ማኅተምና ቼክ እንዲረከቡ በፍርድ ቤት ተወሰነላቸው

የኢዴፓ ፕሬዚዳንት የፓርቲውን ማኅተምና ቼክ እንዲረከቡ በፍርድ ቤት ተወሰነላቸው

ቀን:

የቂርቆስ ምድብ አንደኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ግንቦት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የኢትጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ዋና ጸሐፊ አቶ ሳህሉ ባዩ በእጃቸው የሚገኘውን ማኅተምና ቼክ ለፕሬዚዳንቱ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) እንዲያስረክቡ ወሰነ፡፡

በኢዴፓ አመራሮች መካከል ከገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ጋር እየተካሄደ በነበረው ድርድር ምክንያት፣ በፓርቲው አመራር ማንነት ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት በኢዴፓ አመራር ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ደርሶ ጽሕፈት ቤቱም ለጫኔ ከበደ (ዶ/ር) ዕውቅና እንደሰጠ፣ በፓርቲው አመራሮች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ምክንያት ወደ አመራር የመጡት ግለሰቦች ምርጫ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ያላደረገ በመሆኑ እንደማይቀበለው አስታውቆ ነበር፡፡

ምንም እንኳን ምርጫ ቦርድ ይህን ቢወስንም ተመርጠው የነበሩት የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰና የፓርቲው መሥራችና ነባር አባል አቶ ልደቱ አያሌው፣ ውሳኔው ፓርቲውን የማፍረስ ነው በማለት ተቃውሞ አሰምተው ነበር፡፡

በእነዚህ ውሳኔዎች ከስምምነት ላይ ባለመድረሳቸውና ውዝግቡ መፍትሔ ባለማግኘቱ፣ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ዋና ጸሐፊው የፓርቲውን ማኅተምና ቼክ እንዲያስረክቡ ይወሰንልኝ በማለት ክስ መሥርተው ነበር፡፡

በዚህም መሠረት ጉዳዩን ሲመረምር የቆይው የቂርቆስ ምድብ 1ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ‹‹ተከሳሽ (አቶ ሳህሉ ባዩ) የፓርቲውን ሕጋዊ ማኀተም ከፕሬዚዳንቱና ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዕውቅና ውጪ ያላግባብ መጠቀማቸው የተረጋገጠና ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነትም የታገዱ መሆኑን ከሳሽ ባቀረቡት ማስረጃ ያስረዱ በመሆኑ ደብዳቤ መፈረም፣ እንዲሁም የሒሳብ ወጪዎችን የማዘዝ ሥልጣን የፕሬዚዳንቱ ስለሆነ ተከሳሹ የተረከቡትን የፓርቲውን ማኅተምና የገንዘብ ማንቀሳቀሻ ቼክ ለከሳሽ እንዲያስረክቡ ተወስኗል፤›› በማለት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...