‹‹ማንም ከትግሉ አይወጣም! ከዚያች ከመንግሥት ፔሮል ላይ ሊወጣ ግን ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን ከትግሉ ይወጣል ማለት አይደለም፡፡ ትግሉ እስከ መጨረሻ ይቀጥላል!!››
ነባር የኢሕአዴግ ታጋይ ኅላዌ ዮሴፍ፣ 27ኛው የግንቦት 20 በዓል በመቐለ ከተማ በመድረክ ውይይት ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲከበር የተናገሩት፡፡ በመድረኩ የትጥቅ ትግል መነሻ፣ የግንቦት 20 ፍሬዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በተካሄደበት ወቅት አቶ ኅላዌ፣ በኢትዮጵያ አዲስ ሥርዓት መገንባት መቻሉን ጠቅሰው፣ በሒደት ሥርዓቱን የሚፃረሩ አካሄዶች በኢሕአዴግ ውስጥ መታየታቸውንም ሳይገልጹ አላለፉም።