ሱ ሼፍ ጌታዋ በሪሁን
ጥሬ እቃዎች
- 2 ሲኒ ተለቅሞና ታጥቦ የተቀቀለ ምስር
- 2 ራስ የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 1 የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 1 የሻይ ማንኪያ የሾርባ ቅጠል
- 1 ፍሬ የአትክልት ማጂ መረቅ
- 1/3 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 1 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት ዘይት
- 1/3 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 2 ተቆርጦ የተጠበሰ ዳቦ
አዘገጃጀት
- በድስት ላይ ዘይት በማጋል ሽንኩርት ማቁላት ከዛም ምስር፣ ነጭ ሽንኩርት እና የሾርባ ቅጠል በመጨመር ለ3 ደቂቃ ማሸት
- ከዛም ዱቄት በመጨመር ጥቂት ውሃ በማድረግ ለ3 ደቂቃ ማሸት
- በመቀጠል ግማሽ ሊትር ውኃ በመጨመር ከፍ ባለ እሳት ለ25 ደቂቃ ማንተክተክ
- ከእሳት አውርዶ በረድ ሲል መመገብ