Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርት​ ሚኒስትሩ ስፖርቱ ከተዘፈቀበት አረንቋ እንዲወጣ ‹‹መዋቅር›› ላይ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ጠቆሙ

​ ሚኒስትሩ ስፖርቱ ከተዘፈቀበት አረንቋ እንዲወጣ ‹‹መዋቅር›› ላይ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ጠቆሙ

ቀን:

ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ሥር ሰዶ የቆየውን የወጣቱንና የስፖርቱን ችግር ከመሠረቱ ለመቅረፍ አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ መረባረብ እንደሚያስፈልግ አዲሱ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል በተካሔደው የሁለት ቀን የውይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ ለዓመታት ሲሠራበት የቆየው አስተዳደራዊ መዋቅር የችግሩ ሁሉ መሠረት መሆኑን በመጠቆም በተለይ ስፖርቱ ከተዘፈቀበት አረንቋ እንዲወጣ ከተፈለገ በአስተዳደራዊ መዋቅሩ ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

እንደ ሚኒስትር ሬድዋን፣ ለተመልካች ግራ በሚያጋባ ደረጃ የስፖርቱ አመራሮች በኪራይ ሰብሳቢነትና በሌሎችም እንከኖች ተተብትበው ይገኛሉ፡፡ ከእንግዲህም ስፖርቱ በአገር ወዳድና ቅን አሳቢ በሆኑ ባለሙያዎች ብቻ ሊመራ እንደሚገባው በመግለጽ በእሳቸው የሚመራው ሚኒስቴር አዲስ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት የሚሠራበት ዕድል መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

ጥር 18 እና 19 ቀን 2008 ዓ.ም. በተከናወነው በዚሁ የውይይት መድረክ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማስፈፀም መጀመሪያ ያለውን ‹‹በእከክልኝ ልከክልህ›› የተዋቀረ የአሠራር ሥርዓት አቅጣጫ ማስያዝ እንደሚያስፈልግ ያሳሰቡት ሚኒስትር ሬድዋን፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ጉዳይ ጫፍ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

ሚኒስትሩ በተለይ በስፖርቱ ላይ የሚስተዋለው ‹‹ልቀቅ አለቅም›› ትንቅንቅ ለምንና ቦታው ምን ዓይነት ጥቅም እንዳለው እስካሁን በውል የደረሱበት ነገር ባይኖርም፣ ከእንግዲህ ግን መቀጠል እንደሌለበት ነው ያስገነዘቡት፡፡ ያለውን አሠራር ሲያስረዱ ‹‹ሰዎች ለቦታው ራሳቸውን ለማስመረጥ፣ አልያም የእነሱን አካሔድ የሚከተሉ ለማስመረጥ ሲሯሯጡ ይታያሉ፡፡ አሁንም ቦታው ላይ ያለው ጥቅም ምን እንደሆነ አይታወቅም፤›› ብለው በዚህ ረገድ ያለውን አመለካከት ለመቀየር የሚቻለው ማኅበራትን አልያም ተያያዥነት ያላቸውን አካላት ላይ መረባረብ ሳይሆን፣ መንግሥታዊ መዋቅሩን በመፈተሽ ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ምርጫ ሲደረግ በጊዜ ሒደት የተገደበ፣ ክህሎትና ብቃት ያላቸው ቢያንስ ስፖርቱን ሊደግፉ የሚችሉ መሆን እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

የዚህ ቀጣይ መድረክ ማለትም ለሴክተሩ መገናኛ ብዙኃንና ለሕዝበ ግንኙነት ባለሙያዎች እንዲሁም ለፕሪሚየር ሊግ ክለብ አመራሮችና ለፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ከጥር 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ አዳማ ከተማ ላይ ለሦስት ቀናት ሥልጠናና ተመሳሳይ ውይይት እንደሚከናወን መገለጹ ታውቋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ