የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት የነበሩት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
ለብሔራዊ ባንክ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ምክትል ገዥው የተነሱት ረቡዕ ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የልማትና ጥናት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ሆነዋል፡፡
ምክትል ገዥው በፋይናንስ፣ በገንዘብ ፖሊሲና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ የ28 ዓመታት ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ እንግሊዝ ከሚገኘው የሰሴክስ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡