Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኪራይ ቤቶች ሊገነቡ ነው

ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኪራይ ቤቶች ሊገነቡ ነው

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የቤት ፕሮግራሞች ውስጥ ተካተው የቤት ባለቤት መሆን የገቢ አቅማቸው ለማይፈቅድ የከተማው ነዋሪዎች፣ የኪራይ ቤት ግንባታ እንደሚጀመር የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ባለፈው ሐሙስ ጥር 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ይህንን የመንግሥት ዕቅድ ይፋ ያደረጉት፡፡ ከምክር ቤቱ ውይይት በኋላ በጉዳዩ ላይ ከሪፖርተር ጋር አጭር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ሚኒስትሩ፣ እንደ መንግሥት ፍላጐት ቢሆን ኖሮ ሁሉም ዜጐች የቤት ባለቤት ቢሆኑ የተሻለ ነበር ብለዋል፡፡

አሁን ካለው ሁኔታ በተለይም እየጨመረ ከመጣው የቤቶች ዋጋ ጋር ተያይዞ በ10/90 የቤቶች ፕሮግራም ውስጥ እንኳን መካተት የማይችሉ ነዋሪዎች መኖር፣ መንግሥትን አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ እንደከተተው ገልጸዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ለኮንዶሚኒየም ቤቶች የቀበሌ ቤቶች እየፈረሱ ግንባታ መካሄዱና መክፈል ያልቻሉት ደግሞ የቀበሌ ቤት የማይለቁ መሆናቸው፣ መንግሥት ተተኪ ቤቶች እንዲያቀርብ አስገድዶታል ብለዋል፡፡

‹‹እኛ የምንፈልገው አሁን የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም የቤት ዋጋ እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን የሚያሰፍን ስለሆኑ ነው፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ፍላጎቱ ባይታወቅም በዚህ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ግንባታው እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡

የቤቶቹን ፈላጊዎች ለመለየት ሕዝባዊ ውይይት እንደሚጀመር ተናግረው፣ በአሁኑ ወቅት ጥናት እየተከናወነ መሆኑንና በቅርቡም የዲዛይን ሥራ እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...