Friday, June 9, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳየች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቅና የተነፈጋት ሶማሌላንድ፣ ከኢትዮጵያ 70 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳየች፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በጥያቄው የሚስማማ ከሆነ፣ ሶማሌላንድ በይፋ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀቷን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የዓለም አገሮች እንደ ሉዓላዊ አገር ዕውቅና ባይሰጧትም፣ ራሷን ሉዓላዊ አገር ብላ የምትጠራው ሶማሌላንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎቷን የምታሟላው ከነዳጅ ነው፡፡

ይህም ለሕዝቧ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዓለም ውዱ እንዲሆን ያደረገ ሲሆን፣ አንድ ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በሰዓት አንድ ዶላር ዋጋ እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በዚህ ምክንያት ሶማሌላንድ ትኩረቷን በኢትዮጵያ ላይ በማድረግ፣ ኢትዮጵያ 70 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንድትሸጥላት ፍላጎቷን መግለጿ ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ዕውቅና ሳትሰጥ በተያለዩ ጉዳዮች በትብብር ስትሠራ ቆይታለች፡፡ ኢትዮጵያ ለምሥራቅ አፍሪካና ለአካባቢው አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል የመሸጥ ፍላጎት ቢኖራትም፣ ሶማሌላንድ ዕውቅና የተነፈጋት አገር በመሆኗ የኃይል ሽያጩ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈልግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ኃይል እምብርት ለመሆን በያዘችው ዕቅድ፣ በአካባቢዋ ላሉ አገሮች ኃይል የመሸጥ ግዙፍ ዕቅድ እንዳላት ይታወቃል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ ቀደም ከሱዳን፣ ከጂቡቲና ከኬንያ ጋር የኃይል ሽያጭ ስምምነት መፈጸሟ ይታወቃል፡፡ ስምምነት ከመፈጸም ባሻገር ለአገሮቹ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ጀምራለች፡፡ ከእነዚህ አገሮች በተጨማሪ ከታንዛንያ ጋር የኃይል ሽያጭ ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድር ስታካሂድ ቆይታለች፡፡

በድርድር ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ በመደረሱ ታንዛኒያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ትፈጽማለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከታንዛንያ በተጨማሪ ከሩዋንዳ፣ ከብሩንዲና ከደቡብ ሱዳን ጋር የኃይል ሽያጭ ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድር እየተካሄደ ነው፡፡ የተያዘው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟ 17 ሺሕ ሜጋ ዋት እንደሚደርስ ተመልክቷል፡፡   

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች