Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትሪያትሎን ውድድር በላንጋኖ ተካሄደ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትሪያትሎን ውድድር በላንጋኖ ተካሄደ

ቀን:

በኢትዮጵያ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ከጎዳና ላይ ሩጫ ባሻገር በዓይነቱ ልዩና አዝናኝ የስፖርት ቱሪዝምን ከአካባቢ ጥበቃ ሥራ ጋር በማስተባበር የማስተዋወቅ እንዲሁም ተተኪ አትሌቶችን የማፍራት ዓላማ በማንገብ የተራራ ላይ ውድድር በማዘጋጀት የሚታወቀው ሪያ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የስፕሪንት ትሪአትሎን ውድድር ‹‹ኢትዮ – ትሪያትሎን›› በሚል ስያሜ ጥር 21 እና 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በላንጋኖ ሳባና ሐይቅ ዳርቻ አከናውኗል፡፡ በቀጣዩ ሁለት ዓመት ውስጥ በኦሊምፒክ ስታንዳርድ የምሥራቅ አፍሪካን የትሪአትሎን ሻምፒዮና ማዘጋጀት የሚያስችል ዕቅድ መያዙንም የውድድሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

በአትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም የቦርድ ሰብሳቢነት የተመሠረተው ሪያ ኢትዮጵያ፣ ስፖርት ቱሪዝምን የማስፋፋት ዓላማውን ለማሳካት ባልተለመደ መልኩ በአገሪቱ አዲስ የሆነውን የተራራ ላይ ሩጫ በማዘጋጀት ላለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ቁጥር ያላቸው የውጭ አገር ዜጎችና የአገሪቱ ብርቅዬ አትሌቶች የተሳተፉበት ውድድር በአብጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ወንጪ ሐይቅ ላይ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

ዘንድሮ ደግሞ በኢትዮጵያ በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ልዩ የሆነውን ሦስት የውድድር ዓይነቶችን ማለትም ውኃ ዋና፣ ብስክሌትና ሩጫ በአንድ ላይ በማጣመር ዓለም አቀፍ ይዘት ያለውን የስፕሪንት ትሪአትሎን ውድድር ጥር 21 እና 22 ቀን በላንጋኖ የሐይቅ ዳርቻ አከናውኗል፡፡ የውድድሩ አዘጋጅና የሪያ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃለአብ ጌታነህ ለሪፖርተር በላኩት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ በላንጋኖ ሳቫና የሐይቅ ዳርቻ በተካሄደው ውድድር ላይ በአዋቂዎች ምድብ 97 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ስብጥራቸው ደግሞ 54 ተወዳዳሪዎች (ሴቶች 16፣ ወንዶች 38) እንዲሁም 43 ተወዳዳሪዎች (ሴቶች 10፣ ወንዶች 33) በቡድን ተሳትፈዋል፡፡

ውድድሩ የሸፈነው ርቀት 750 ሜትር የሐይቅ ላይ ዋና፣ 20 ኪሎ ሜትር ብስክሌትና አምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር መሆኑ ተገልጿል፡፡ የውድድሩ አንድ አካል በነበሩት የሕፃናት ምድብ ደግሞ በሁለት የዕድሜ እርከን ማለትም ከሰባት እስከ አሥር እና ከ11 እስከ 14 ተከፍሎ በድምሩ 33 ሕፃናት ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ከነዚህም 13ቱ በቡድንና 13 ደግሞ በነጠላ የተደረገ ውድድር መሆኑ ተነግሯል፡፡ ውድድሩ የሸፈነው ርቀትም ለመጀመርያዎቹ ሕፃናት 100 ሜትር የሐይቅ ላይ ዋና፣ 1.5 ኪሎ ሜትር ብስክሌትና 750 ሜትር ሩጫ ሲሆን፣ በሁለተኛው የዕድሜ ምድብ ላሉት 200 ሜትር የሐይቅ ላይ ዋና፣ ስድስት ኪሎ ሜትር ብስክሌትና ሦስት ኪሎ ሜትር ሩጫ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በውድድሩ 90 በመቶው በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች የተሳተፉበት ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጭምር ተገልጿል፡፡ የውድድሩ አዘጋጅ ሪያ ኢትዮጵያ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ዝናና ተወዳጅ የሆነው የትሪያትሎን ስፖርትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት በዓመት አንድ ጊዜ በቋሚነት በአገሪቱ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች ለማከናወን ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡ ስፖርቱ የበለጠ ተስፋፍቶ በኅብረተሰቡ ዘንድ ተደራሽ መሆን ይችል ዘንድ፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽንና ውኃ ዋና ፌዴሬሽን ትኩረት እንዲሰጡት ጭምር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይህንን የስፕሪንት ትሪያትሎን ውድድር በአፍሪካ ደረጃ ደቡብ አፍሪካ በምሥራቅ አፍሪካ ደረጃ ደግሞ ኬንያ በሻምፒዮና ደረጃ በየዓመቱ እንደሚያከናውኑት አቶ ቃለአብ ጌታነህ ገልጸዋል፡፡

ስፖርቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ 3.86 ኪሎ ሜትር ውኃ ዋና፣ 180 ኪሎ ሜትር ብስክሌትና 42 ኪሎ ሜትር ሩጫ እንደሚሸፍን ተወዳዳሪዎቹም ‹‹አይረን ማን›› በመባል እንደሚታወቁ ጭምር አዘጋጁ ተናግሯል፡፡

    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...