Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትሉሲዎች ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ይጫወታሉ

  ሉሲዎች ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ይጫወታሉ

  ቀን:

  ‹‹ከእንግዲህ ትግሉ ለተሳትፎ ሳይሆን ለውጤት ነው›› አቶ ብርሃኑ ግዛው፣ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎች) ዋና አሠልጣኝ

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀነ ገደቡ የተሳትፎ መልስ ባለመስጠቱ ምክንያት በ2009 ዓ.ም. በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሳይካተት የቀረው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በመጪው የካቲት በሚጀመረው ማጣሪያ እንዲካፈል የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ወስኗል፡፡ ከአንድ ወር በኋላ ከአልጀሪያ አቻው ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡ የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድንም በተመሳሳይ ለ2009ኙ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የአልጀሪያ አቻውን ይገጥማል፡፡

  የካፍን ውሳኔ ተከትሎ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እንዳስታወቀው፣ ካፍ ለዚህ ውሳኔ የበቃው ቀደም ሲል ለማጣሪያው ተመዝግቦ የነበረው የቶጎ ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ መውጣቱን ተከትሎ የተገኘ ተሳትፎ ነው፡፡ ሆኖም ቀደም ሲል ፌዴሬሽኑ ለጥፋቱ ተጠያቂ ያደረጋቸውን ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የዲሲፕሊን ዕርምጃ መውሰዱ ይታወሳል፡፡

  የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሴቶች ብሔራዊ ቡድን ምዝገባ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን የአሠራር ችግር በክፍተትነቱ ወስዶ ነገር ግን የሉሲዎች ተሳትፎ እንዲቀጥል ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት በተለይም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት በካይሮ የካፍ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም በሩዋንዳ ኪጋሊ የቻን ውድድር ወቅት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የካፍ ኃላፊዎች በማነጋገር ያከናወኑት ዲፕሎማሲያዊ ተግባር የሚፈለገውን ውጤት ማስገኘቱንም የፌዴሬሽኑ መግለጫ አብራርቷል፡፡

  በዚሁ መሠረት በቅርቡ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩት ሉሲዎቹ የመጀመርያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጭ በአልጀርስ የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. የመልሱን ጨዋታ ደግሞ መጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እንደሚያከናውኑ ይጠበቃል፡፡ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት  ድርጅት (ኢጋድ) አባል አገሮች በአምስት የስፖርት ዓይነቶች ከጥር 8 እስከ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ጂቡቲ ላይ ሊያከናውኑት በነበረው ስፖርታዊ ውድድር ላይ ለሉሲዎቹ ዋና አሠልጣኝ ሆነው የተሾሙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ ዋና አሠልጣኝ አቶ ብርሃኑ ግዛው እንዲቀጥሉ ፌዴሬሽኑ ለአሠልጣኙ መመርያ መስጠቱ ተሰምቷል፡፡ አቶ ብርሃኑም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም ተሳታፊ አገሮች በእግር ኳስ ብቻ ለመሳተፍ ባሳዩት ፍላጎትና ምክንያት ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ስለመደረጉም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

  የሉሲዎቹን ወደ ውድድር መመለስን አስመልክቶ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው አሠልጣኝ ብርሃኑ፣ ‹‹ከእንግዲህ ትግሉ ከተሳትፎ ለምን ወጣን ሳይሆን ለውጤት ነው፤›› ብለው ለዚህ ስኬት ለታገሉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ መገናኛ ብዙኃኑና ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ምስጋና አቅርበዋል፡፡

  መደበኛውን ዝግጅት ከተወሰኑ ቀናት በኋላ እንደሚጀመር የተናገሩት አሠልጣኙ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከወትሮው በተለየ አሠራር ዕድሜያቸው ከ17 እና ከ20 እንዲሁም ለኢጋድ አባል አገሮች ተሳትፎ ከ18 ዓመት በታችና ከነባሩ ዋናው ብሔራዊ የተካተቱበት ምርጫ አድርጎ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጠንካራ ቡድን ይዞ ለመቅረብ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

  ሉሲዎቹ የአልጀሪያ አቻቸውን በደርሶ መልስ የሚያሸንፉ ከሆነ ከኬንያና ኮንጎ ኪንሻሳ አሸናፊ ጋር ለመጨረሻው ማጣሪያ ይጫወታሉ፡፡

  በጂቡቲ አስተናጋጅነት በአምስት የስፖርት ዓይነቶች ማለትም በሴቶች እግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስና በጠረጴዛ ቴኒስ ውድድሮችን ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡ ኢትዮጵያያን በመወከል ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በእግር ኳስ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በወቅቱ በዋና አሠልጣኝነት የተቀጠሩት አቶ ብርሃኑ ግዛው ኮንትራታቸው እስከ መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ መሆኑ ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...