Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ አንበሶች እንደሚኖሩ ተረጋገጠ

በአላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ አንበሶች እንደሚኖሩ ተረጋገጠ

ቀን:

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው አላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ አንበሶች እንደሚኖሩ ተረጋገጠ፡፡ በፓርኩ አንበሶች እንደሚኖሩ ለመጀመርያ ጊዜ የተረጋገጠው ቦርን ፍሪ ኦርጋናይዜሽን ከኦክስፎርድ ዩኒቭርሲቲ የዱር እንስሳት ጥበቃ ጋር በመተባበር ባደረገው አሰሳ ነው፡፡

በቦርን ፍሪ ድረ ገጽ እንደተገለጸው፣ የአንበሶቹ መኖር የታወቀው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው አላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በታዋቂው የአናብስት ጥበቃ ባለሙያ ዶ/ር ሀንስ ባውር በተደረገው አሰሳ ነው፡፡

ከአዲስ አበባ 1025 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኘውና በርካቶች የመጎብኘት ዕድሉን ባላገኙበት የአላጥሽ ፓርክ፣ አንበሶች ለዓመታት እንደኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ቢያውቁም፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በይፋ አልተገነዘበም ነበር፡፡ ኢንተርናሽናል ዩኒየን ፎር ኮንሰርቬሽን ኦፍ ኔቸርም (አይዩሲኤን) ፓርኩ ውስጥ የአንበሳ ዝርያዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከመገመት የዘለለ መረጃ አልነበረውም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዶ/ር ሐንስና የጥናት ቡድናቸው የተደረገው ምርምር በአካባቢው አንበሶች እንደሚኖሩ አረጋግጧል፡፡ በካሜራ የተቀረፁ የአንበሶቹ ምስልና በአካባቢው የተውት ዳና ያለ ምንም ጥርጥር ስለመኖራቸው ያስረዱ መረጃዎች ናቸው፡፡ አላጥሽ ፓርክ የሚገኘው በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ሲሆን፣ የጥናት ቡድኑ ከአላጥሽ ውጪ በሱዳን በሚገኘው ዲንደር ናሽናል ፓርክ ውስጥም አንበሶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ደምድሟል፡፡

ዶ/ር ሀንስ እንደተናገሩት፣ አላጥሽ ፓርክ ውስጥ አንበሶች ስለመኖራቸው ከዚህ ቀደም በተካሄዱ አህጉራዊ ወይም ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ባይገለጽም በፓርኩ እንዲሁም በሱዳኑ ዲንደር ፓርክ ውስጥ አንበሶች መኖራቸው ሙሉ በሙሉ ተረጋግጧል፡፡

‹‹የአንበሶችን መኖር የሚያሳዩ ምልክቶች ስለ እንስሳቱ መኖር አመላክተውናል፡፡ አካባቢው እርጥበታማ በመሆኑ አንበሶች ይመርጡታል፡፡ የአንበሶቹ ቁጥር በፓርኮቹ ካለው እርጥበት አንፃር ሲታይ በ100 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ሜርት አንድ ወይም ሁለት አንበሳ ሊኖር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በ10,000 ኪሎ ሜትር ስኰዌር ርቀት ደግሞ ከ100 እስከ 200 አንበሶች እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ ከእነዚህ መካከል ከ27 እስከ 54 የሚሆኑ አንበሶች በአላጥሽ ይኖራሉ ማለት ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በአይዩሲኤን፣ አደጋ ያንዣበበባቸው እንስሳት ዝርዝር ውስጥ የአፍሪካ አንበሶች ግንባር ቀደሙን ቦታ ይይዛሉ፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1980 ወዲህ የአንበሳ ዝርያዎች ቁጥር ከ70 በመቶ ወደ 50 በመቶ ወርዷል፡፡ በአጠቃላይ አፍሪካ ውስጥ ደግሞ ወደ ስምንት በመቶ ያህል ቦታ ላይ ብቻ ይኖራሉ፡፡ ሱዳን ውስጥ አንበሶች ለመጥፋት እንደተቃረቡ ይታሰብ ስለነበር ግኝቱ ለአገሪቱ አበረታች ነው፡፡ መኖራቸው የተረጋገጠው እነዚህ አንበሶች ህልውና አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከኢትዮጵያና ሱዳን መንግሥት ጋር በመነጋገር የሚሠሩ ሥራዎች እንደሚኖሩም የቦርን ፍሪ ድረ ገጽ ያትታል፡፡

የቦርን ፍሪ ፋውንዴሽንና የቦርን ፍሪ ዩኤስኤ ዋና ሥራ አስኪያጅ አዳም ኤም ሮበርትስ የአንበሶቹ መገኘት በጣም አስደሳች ዜና እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በመላው አፍሪካ የአንበሶች ቁጥር መቀነሱ የሚገለጽበት ወቅት በመሆኑ ግኝቱ ጠቀሜታ አለው፡፡ ለአንበሶች ጥበቃ መንግሥት ተባባሪያችን በሆነባት ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘታቸውም ጥቅሙን ያጎላዋል፡፡ አንበሶቹ ለመጠበቅ የምንችለውን ሁላ ማድረግ አለብን፡፡ የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው መልካም እንዲሆን በተቀሩት የአፍሪካ አገሮች ላሉትም አንበሶች ጥበቃ መደረግ አለበት›› ብለዋል፡፡

የአንበሶቹ መገኘት ቦርን ፍሪ 2016 ዓመትን ‹‹ዘ ይር ኦፍ ዘ ላየን›› (የአንበሳ ዓመት) ብሎ በሰየመበት እንዲሁም ኦስካር ያሸነፈው ፊልም ‹‹ቦርን ፍሪ›› 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ወቅት ነው፡፡

የቦርን ፍሪ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዘለዓለም ተፈራ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአንበሶቹ መኖር በይፋ መታወቁ በመንግሥት አስፈላጊው ጥበቃ  እንዲደረግላቸው የሚያነሳሳ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የአፍሪካ አገሮች የአንበሶች ቁጥር መመናመኑ አደን እንዲቆም በማድረግና በሌሎችም መንገዶች ዕርምጃ እንዲወሰድ ማነሳሳቱን ገልጸዋል፡፡ በአላጥሽ አካባቢ የሚኖሩት አንበሶች የተለያዩ አደጋዎች እንደተጋረጡባቸውና ለወደፊት አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው መልካም አጋጣሚ እንደተፈጠረም ያምናሉ፡፡

የዱር እንስሳት (የአንበሶችን ጨምሮ) የሚመገቡት ነገር በማጣት ወደ ነዋሪዎች ክልል ለመግባት ሲገደዱ፣ ነዋሪዎች ራሳቸውንና ከብቶቻቸውን ለመከላከል አንበሶቹ ላይ ጥቃት ያደርሳሉ፡፡ ይህ በአካባቢው ከሚስተዋሉ ተግዳሮቶች አንዱ ሲሆን፣ ለዱር እንስሳት የተከለሉ ቦታዎች ጥበቃ እንዲደረግ በማነሳሳት ረገድ የአላጣሽ አንበሶች መገኘት ሚና እንደሚኖረው ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...