Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበአፍሪካ ለታዳጊዎች ሞት ቀዳሚ ምክንያት ኤድስ መሆኑ ተገለጸ

  በአፍሪካ ለታዳጊዎች ሞት ቀዳሚ ምክንያት ኤድስ መሆኑ ተገለጸ

  ቀን:

  አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በማድረግ ውጤት ማስመዝገብ ቢችሉም፣ በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አፍሪካውያንን ከኤችአይቪ ለመታደግ የተሠራው ሥራ ይህን ያህል ለውጥ አለማሳየቱን የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ድርጅት አስታወቀ፡፡

  በታዳጊዎች ዙሪያ የሚሰጠው አጠቃላይ የኤችአይቪ ምርመራ፣ ለታማሚዎች የሚደረግ ዕርዳታ፣ እንክብካቤ እንዲሁም ሕክምናውን ለማሳደግ የተደረገው ጥረት አናሳ መሆኑ የተፈለገውን ያህል ለውጥ ለማምጣት እንቅፋት መሆኑን፤ ይህም ኤችአይቪ ከ10 እስከ 19 ዓመት ድረስ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ቀዳሚ የሞት ምክንያት እንዲሆን ማድረጉን ጨምሮ ገልጿል፡፡

  በታዳጊዎች ላይ ለውጥ ለማምጣትና ችግሩን ለመቅረፍም፣ የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ድርጅት በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከዓለም ጤና ድርጅትና ከአምሬፍ ጋር በጋራ ለመሥራት ቅዳሜ ጥር 21 ቀን 2008 ዓ.ም. የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ በዕለቱም በሌሎቹ የዕድሜ ክልሎች ማስመዝገብ የተቻለውን ለውጥ በታዳጊዎች ላይ ማምጣት ያልተቻለው፣ ከትኩረት ማነስ እንደሆነ፣ በተለይም ከሰሃራ በታች በሚገኙ ታዳጊ ሴቶች ላይ ችግሩ የከፋ መሆኑም ተገልጿል፡፡   

  ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ድርጅት የኤችአይቪንና የካንሰር በሽታን ለመቆጣጠር በርካታ ጥረቶች ሲያደርግ ቆይቷል፣ ይሁን እንጂ የተፈለገውን ያህል ውጤት ማስመዝገብ አልተቻለም፡፡ በተለያዩ በተላላፊና በማይተላለፉ በሽታዎች የሚሞቱ አፍሪካውያን ቁጥር ብዙ ነው፡፡ ይህም ትልቅ የቤት ሥራ መኖሩን ያመለክታል፡፡

  የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እ.ኤ.አ. በ2015 በኤችአይቪ የሚያዙ ሕፃናትን ቁጥር ለመቀነስ የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት ሥርጭቱን ለመቆጣጠር መሥራቱን የተናገሩት የድርጅቱ የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር ዶ/ር ሙስጠፋ ካሎኮ ናቸው፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ፣ በድርጅቱ ጥረት በኤችአይቪ የሚጠቁ ሕፃናትን ቁጥር መቀነስ ተችሏል፡፡ በቀጣይም ሥርጭቱን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች በኅብረት መሥራት አለባቸው፡፡

  የኤችአይቪን ሥርጭት ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መሥራት ግድ ነው የሚሉት የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ድርጅት ፕሬዚዳንትና የጋና ቀዳማዊት እመቤት ዶ/ር ናና ሎርዲና ናቸው፡፡

  አንድም ሕፃን በኤችአይቪ እንዳይያዝና የተሻሻለ የወጣቶች የሥነ ተዋልዶ ጤናና መብት ለማስጠበቅ መሥራት ወሳኝ ቢሆንም፣ የአቅም ማነስ፣ አመቺ ያልሆኑ ፖሊሲዎች ደንቦችና የመሳሰሉት ችግሮች መኖር የተፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ አላስቻሉም፡፡ በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ ከሥነ ተዋልዶ ጤና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና የባለድርሻ አካላት አቅም የማጠናከር ሥራም መጐልበት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

  ከተቋቋመ ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ድርጅት 40 አባላት አሉት፡፡ ለጥቃት ለተጋለጡ የማኅበረሰቡ አካላት ድምፅ በሚል የተቋቋመው ድርጅቱ ሴቶችና ሕፃናት በኤችአይቪ እንዳይጠቁ የተለያዩ ሥራዎች ይሠራል፡፡   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...