Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየአካባቢ ፖሊሲ ክለሳ በዘንድሮ ማብቂያ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

የአካባቢ ፖሊሲ ክለሳ በዘንድሮ ማብቂያ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

ቀን:

ክፍተቶች አሉበት የተባለው ብሔራዊ የአካባቢ ፖሊሲ እየተከለሰ መሆኑና ሥራው በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ተጠናቆ በረቂቅ ደረጃ ይወጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ፡፡

አቶ አዲሱ ገብረመድህን የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ሲኒየር ኢንቫይሮመንታል ኮንሰርቬሽን ኤክስፐርት እንደገለጹት፣ ክለሳው የሚካሄደው ከዘርፎች፣ ከምርምር ተቋማትና ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ሙያተኞችን ባቀፈው ኮሚቴ አማካይነት ነው፡፡

ክለሳው ያስፈለገበት ምክንያት ፖሊሲው ከወጣ ከ15 ዓመት በላይ ስላስቆጠረና በአሁኑ ጊዜም ብዙ ከፍተቶች ስላሉበት ነው፡፡ አገሪቱ ከአሁን በፊት የአካባቢ ስትራቴጂ ስላልነበራትም የአካባቢ ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

በሥራ ላይ ያለው ፖሊሲ በአገሪቱም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን አዳዲስ ክስተቶች ያላካተተ ነው፡፡ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ፣ የበካይ ጋዝ ልቀት፣ አገሪቷ ያደረገቻቸው የአካባቢና ደን ስምምነቶች፣ በከተሞች ለአየር ብክለት ለውጥም ሆነ ለእምቅ ጋዞች መጨመር ምክንያት የሆኑ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች፣ የትራንስፖርት እንዲሁም ተያያዥ ዘርፎች አልተካተቱበትም፡፡ የዱር እንስሳት አያያዝ፣ የግሉ ዘርፍ የሚኖረው ሚናም አልተቃኘም፡፡ በመሆኑም እነዚህንና ተያያዥ ጉዳዮችን ለማካተት የቀድሞው ፖሊሲ እየተከለሰ ይገኛል፡፡

የአካባቢና ደን ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ባካሄደው ውይይት፣ በሥራ ላይ ያለው የአካባቢ ፖሊሲ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር፣ ክፍተቶች እንዳሉበትና መሻሻል እንደሚያስፈልገው አሳውቆ ነበር፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን ከልቀት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ትራንስፖርት፣ ከተማ ልማት፣ የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች በአምስት ዓመት ውስጥ እንደርስበታለን ብለው ባወጡት እቅድ ውስጥ ወይም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ማካተታቸውንም አቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡

ይህንንም ለማስፈጸም፣ በስትራቴጂው ዙሪያ ላይ ያተኰረ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን አማካይነትም ሥልጠናና አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

እንደ ኤክስፐርቱ ማብራሪያ፣ ክልሎችና ዞኖች ወረዳዎችም ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ ባካሄዱት እንቅስቃሴ ውስጥ ክፍተቶች ታይቶባቸው ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ስትራቴጂውን ከአምስት ዓመቱ እቅድ ጋር ለማካተት የሚያስችል ፕላን አለማውጣት፣ ለሀብት ማሰባሰብ የሚረዳ ወይም እገዛ የሚያደረግ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል አለመቅረጽ፣ ከቁጥጥርና ግምገማ ጋር የተያያዘ እንቅፋት እንዲሁም ተቋማዊ አደረጃጀት ላይ የተከሰቱ ክፍተቶች ይገኙበታል፡፡ እስከ ታች ድረስ በአንድ ዘርፍ አለመሄድም ሌላው ችግር ነው፡፡

ለምሳሌ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በፌዴራል ደረጃ ራሱን ችሎ ቢደራጅም፣ ወደ ክልል ዞንና ወረዳ ሲወርድ ከኢንዱስትሪ ወይም ከከተማ ልማት ጋር ተቀላቅሎ ይገኛል፡፡ የአካባቢው ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴርም በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ከግብርናና ከመሬት አጠቃቀም በአጠቃላይ ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ተቀላቅሎ ይገኛል፡፡

ይህ ዓይነቱ አደረጃጀት፣ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ማነቆ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም የተዘረዘሩትን ችግሮች ለመፍታት፣ ለክልሎች፣ ለዞኖችና ለወረዳዎች ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ የአምስት ዓመት ብሔራዊ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክትም ተቀርጿል፡፡ በፕሮጀክቱም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ያሉባቸውን ክፍተቶች በመጠየቅ የሥልጠና ማኑዋል መዘጋጅቱንና የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንደሚሰጥ ኤክስፐርቱ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2002 ዓ.ም. የካርቦንዳይኦክሳይድ የልቀት መጠኗ 150 ሚሊዮን ቶን እንደነበር፣ በዛን ጊዜ በነበረው አካሄድ የምትቀጥል ከሆነም በ2022 ዓ.ም. የልቀት መጠኑ 400 ሚሊዮን ቶን እንደሚደርስም ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በትክክል ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ በ2022 ዓ.ም. 400 ሚሊዮን ይደርሳል ከተባለው የልቀት መጠን ውስጥ 255 ሚሊዮን ቶን ካርቦንዳይኦክሳይድ በመቀነስ፣ መጠኑ 145 ሚሊዮን ቶን እንዲሆን ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡   

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...