Sunday, December 3, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአዋሽ ባንክ የተከፈለ ካፒታሉ 2.16 ቢሊዮን ብር ደረሰ

ተዛማጅ ፅሁፎች

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ወደ 2.16 ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ ከግል ባንኮች በተከፈለ ካፒታል መጠን ቀዳሚ ሊሆን መቻሉን ገለጸ፡፡ ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባንኩ የካፒታል መጠኑን ከፍ ያለው በተለይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የባንኩ ባለአክሲዮኖች ተጨማሪ አክሲዮኖች ግዥ በመፈጸማቸው ነው፡፡ የባንኩ የ2007 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የተከፈለ ካፒታል መጠኑ 1.77 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ የበጀት ዓመቱ ሒሳብ ከተዘጋ በኋላ በተለይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በርካታ ባለአክሲዮኖች የ2007 በጀት ዓመት የትርፍ ድርሻቸውን ሲቀበሉ ለካፒታል ማሳደጊያ በማዋላቸው፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 2.16 ቢሊዮን ብር ሊደርስ መቻሉን አመልክቷል፡፡ እንደ ባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ባንኩ አሁን የደረሰበት የተከፈለ ካፒታል መጠን ከግል ባንኮች ከፍተኛው እንዲሆን የሚያስችለው ነው፡፡ ባንኩ ከሁለት ዓመታት በፊት የተፈቀደ ካፒታሉን ወደ ሦስት ቢሊዮን ብር እንዲያደግ በወሰነበት ወቅት፣ ይህንን የተከፈለ ካፒታል መጠን በአምስት ዓመታት ውስጥ ለማሟላት አቅዶ ነበር፡፡ አሁን ግን እየታየ ባለው የካፒታል ዕድገት መሠረት ሦስት ቢሊዮን ብሩን በሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ እንደሚቻልም የባንኩ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፈው ዓመት ከታክስ በፊት 861 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ በአገሪቱ ያሉት 16ቱ የግል ባንኮች በጠቅላላ የተከፈለ ካፒታላቸው ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ ባንኩ ከ3,500 በላይ ባለአክሲዮኖችን የያዘ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ከ220 በላይ ቅርንጫፎች አሉት፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች