Sunday, February 25, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከፋይናንስ ተቋማት ውጭ ላሉ አክሲዮን ኩባንያዎች መቆጣጠሪያ ሕግ እየተዘጋጀ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከፋይናንስ ተቋማት ውጭ ያሉ የአክሲዮን ኩባንያዎችን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ ሕግ በዚህ በጀት ዓመት ለማፅደቅ ዝግጅት እየደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከባንክና ከኢንሹራንስ ውጭ ያሉ የአክሲዮን ኩባንያዎችን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለው ረቂቅ ሕግ እየተዘጋጀ ያለው በንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡

በአንዳንድ የአክሲዮን ኩባንያዎች ውስጥ እየታዩ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ያስችላል የተባለው ረቂቅ ዝግጅት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ፣ ከባንክና ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውጭ ያሉ የአክሲዮን ኩባንያዎችን ጉዳይ የሚከታተል ራሱን የቻለ ዳይሬክቶሬት እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

ረቂቅ ሕጉንም እየተዘጋጀ ያለው በዚሁ ዳይሬክቶሬት በኩል መሆኑን የዳይሬክተሩ ዳይሬክተር በመሆን የተሰየሙት አቶ አየነው ፈረደ ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ አየነው ገለጻ፣ ንግድ ሚኒስቴር ይህንን ዳይሬክቶሬት ሊያቋቋም የቻለው በአክሲዮን ኩባንያዎች ላይ የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ  ነው፡፡

በዚሁ መነሻነት አሉ የተባሉትን ክፍተቶች ለመሙላት የብሔራዊ ብሔራዊ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ባንኮችን እንደሚቆጣጠርበት ዓይነት ሕግ ማዘጋጀት በማስፈለጉ የሕጉ ረቂቅ እየተዘጋጀ ሲሆን፣ ለመንግሥት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ሥራ ላይ እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

ሕጉ የአክሲዮን ኩባንያዎች ጤናማ ሆነው እንዲጓዙ ከማስቻሉም በላይ በተለይ ኩባንያዎች ተወዳዳሪ ሆነው እንዲጓዙ ለማስቻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በአክሲዮን ደረጃ ከተቋቋሙ ኩባንያዎች ውስጥ እስካሁን ውጤታማ ሆነዋል ተብለው የሚታመኑት ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሲሆኑ፣ ለዚህ ውጤት የበቁትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚያደርገው ቁጥጥር እንደሆነ በተለያዩ መድረኮች ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ከፋይናንስ ተቋማቱ ውጭ ያሉ የአክሲዮን ኩባንያዎች እንዲተዳደሩበት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሕግም፣ ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመቆጣጠሪያ ስልቶች እንደ ሞዴል ይጠቀማል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች