Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየመኢአድ ፕሬዚዳንት የፓርቲውን ማኅተም እንዳይጠቀሙ በፍርድ ቤት ታገዱ

  የመኢአድ ፕሬዚዳንት የፓርቲውን ማኅተም እንዳይጠቀሙ በፍርድ ቤት ታገዱ

  ቀን:

  የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምደብ ሦስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ የፓርቲውን ማኅተም እንዳይጠቀሙ ጥር 25 ቀን 2008 ዓ.ም. አገደ፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህን ዕግድ ያስተላለፈው ባለፈው ሳምንት የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ያገደው የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ባቀረቡት ክስ መሠረት ነው፡፡ ‹‹በከሳሽ ስም የተቀረፀው ማኅተም ተለዋጭ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤቱ እስኪሰጥ ድረስ ተከሳሽ እንዳይጠቀሙበት ታግዷል፤›› በማለት የዕግድ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመመልከት ለየካቲት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ እስከዚህ ቀን ድረስ ፕሬዚዳንቱ የፓርቲውን ማኅተም እንዳይጠቀሙ ወስኗል፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አበበ የክስ ቻርጅና የዕግድ ደብዳቤው እንደደረሳቸው ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ‹‹የወጣው ዕግድ አግባብ አይደለም፤›› በማለት ዕግዱን ተቃውመዋል፡፡ ‹‹የፍርድ ቤት ደብዳቤ በመሆኑ ዕግዱንና የክስ ቻርጁን ተቀብለናል፡፡ ነገር ግን የተቀጠረበት ቀን የራቀ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲታይልን አቤቱታ አቅርበናል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ አቶ ሙሉጌታ በክስ መዝገቡ ላይ ከሳሽ መኢአድ ተከሳሽ ደግሞ አቶ አበባው መሐሪ ሆነው መቅረባቸው አግባብነት የሌለው እንደሆነ ገልጸው፣ ‹‹ከሳሽና ተከሳሽ ተለያይተው የማይታዩ ናቸው፤›› በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ከሥልጣን ያገደውን የላዕላይ ምክር ቤት ጉዳይን በተመለከተ፣ ‹‹ድርጅቱ እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት አያውቀውም፤›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱን አገድን የሚሉት ግለሰቦች ፓርቲው የማያውቃቸውና ከፓርቲው በዲሲፕሊን ግድፈትና በራሳቸው ጊዜ የለቀቁ ግለሰቦች በመሆናቸው፣ ፓርቲው ዕገዳውን እንደማይቀበለው አመልክተዋል፡፡ አቶ ሙሉጌታ ፕሬዚዳንቱን የማንሳት ሥልጣን ያለው ጠቅላላ ጉባዔው እንጂ፣ 105 አባላት ያሉት የላዕላይ ምክር ቤት እንዳልሆነም አስገንዝበዋል፡፡ የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት እስከሚቀጥለው ጠቅላላ ጉባዔ ድረስ ፕሬዚዳንቱን በማገድ፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ እንድሪያስ ኤሮ ፓርቲውን በጊዜያዊነት እንዲመሩ መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...