ፎቅ በፎቅ ደረቡ
መርቸዲዝ ተንጋለሉ
በቄሳሩ መዲና ናጠጡ ሸለሉ
ሰርቀው እንዳልከበሩ
ገርፈው እንዳልበሉ
አሰቃይተው ያመለጡ ሁሉ
ተደባለቁን በየሠርጉ
በየስደት ቤቱ
ለሙሾው በየቀብሩ
አልቅሰው ሊያላቅሱን
አብረውን ሊጨፍሩ
ተፅዕኖ ሆነና ያለፈን መወደስ
ወኔ ጠፋና ከህሊና ለመዋቀስ
ንፅህና ደብቦ፣ እውነት እንዳይካስ
መርሳት ልማድ ሆኖ አይከፉት – ክፋት ሲደርስ
እንዳልጋጡን ሁሉ አብረውን ሲበሉ
የተበሉትም ብር ብለው ጨፈሩ
- ሰሎሞን ዴሬሳ ‹‹ዘበት እልፊቱ ወለሎታት››