Friday, July 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ወደ ሌላ ተቋም ተዛወሩ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ቺፍ ኢኮኖሚስት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር)፣ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ ልማትና ምርምር ኢንስቲትዩት ተዛወሩ፡፡

ከምክትል ገዥነታቸው ተነስተው ወደ ኢንስቲትዩቱ የመዛወራቸው ዜና ያልተጠበቀ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከ20 ዓመታት በላይ ሲያገለግሉ፣ በምክትል ገዥነትና በቺፍ ኢኮኖሚስት የቆዩት ለስምንት ዓመታት ነው፡፡

በብሔራዊ ባንክ ውስጥ ቁልፍ የሚባለውን የኃላፊነት ቦታ ይዘው የቆዩት ምክትል ገዥው፣ በአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረጉ ተደራራቢ መመርያዎች እንዲወጡ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል፡፡

በዚህ ተግባራቸውና በተለይ በአገሪቱ ባንኮች ላይ ያሳደሩ ነበር በሚባለው ተፅዕኖ ምክንያት፣ በተለይ ከግል ባንኮች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሻካራ እንደነበረም ይነገራል፡፡

አሁን በተመደቡበት ኢንስቲትዩት ቦታ በዋና ዳይሬክተርነት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ በቅርቡ በጡረታ የተገለሉት አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

ዮሐንስ (ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት ባለፈው ዓመት ነው፡፡ ከብሔራዊ ባንክ በተጨማሪ በንግድ ሚኒስቴር ውስጥ ለተወሰኑ ዓመታት ማገልገላቸው ይጠቀሳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥነትን የሚረከበው ቀጣይ ተሿሚ ግን አልታወቀም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች