Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበቦሌ ክፍለ ከተማ የሰሚት አካባቢ ነዋሪዎች ሕገወጦች መግቢያ መውጫ አሳጡን አሉ

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሰሚት አካባቢ ነዋሪዎች ሕገወጦች መግቢያ መውጫ አሳጡን አሉ

ቀን:

‹‹ከወረዳው አቅም በላይ በመሆናቸው ለሚመለከተው አሳውቀናል››

የወረዳ 8 ሥራ አስፈጻሚ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰሚት ማዞሪያ ከተባበሩት ነዳጅ ማደያ ወደ ሰሚት ለስላሳ ማምረቻ ፋብሪካ መውረጃ መንገድ መጋጠሚያ ላይ ‹‹ተደራጅተናል›› የሚሉ ግለሰቦች አካባቢውን መኪና ማሳደሪያና መፀዳጃ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ፣ መሸት ሲል ሰርቆ መደበቂያ በማድረጋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መውጫ መግቢያ ማጣታቸውን ገለጹ፡፡ የአካባቢው ወረዳ 8 ሥራ አስፈጻሚ ደግሞ ድርጊቱ ከአቅም በላይ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል ብለዋል፡፡

- Advertisement -

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እና ወረዳ 8 አካፋይ ላይ ለባቡር ሐዲድ መገንቢያ በተተወ 30 ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ላይ፣ 100 የሚደርሱ የተለያዩ ማሽኖችና ተሽከርካሪዎች ያድራሉ፡፡ ማሽኖቹ ቀደም ብለው በየካ ክፍለ ከተማ አፍሪካ ኤግዚቢሽን ማዕከል መሥሪያ ቦታ ላይ ተከማችተው የነበሩ ናቸው፡፡ ቦታውን ከንቲባ ድሪባ ኩማ ሊመርቁ በተገኙበት ወቅት ለጊዜያዊ ማቆሚያ ማሽኖቹን ወደ ክፍለ ከተማው ያዛወሩ ቢሆንም፣ ‹‹ተደራጅተናል›› በማለት በሕገወጥ መንገድ ተሽከርካሪዎቹ ባሉበት ቦታ እንዲቆሙ ማድረጋቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

አቶ ፍሰሐ ገብሬ፣ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ ይፍሩና አቶ ዳዊት ቀለመወርቅ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች አካባቢውን አረንጓዴ በማድረግ ለራሳቸውና ወደ አካባቢው ለሚመጡ እንደ ማረፊያና መዝናኛ እንዲያገለግል ያለሙት ቢሆንም፣ አሁን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ መፀዳጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተለያዩ የኮንስትራክሽንና ሌሎች ማሽኖችና ተሽከርካሪዎችን በእያንዳንዱ በቀን 50 ብር እያስከፈሉ ማደሪያ በማድረግ፣ አካባቢው መልካም ገጽታውን እንዲያጣና ለባቡር መተላለፊያ ለተተወው ቦታ የተሠራውን ማቀፊያ (ከርቭ) እያፈራረሱት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ማሽኖቹን ለመጠበቅ የሚያድሩት በርካታ ግለሰቦች የሚፀዳዱት በአረንጓዴው ቦታ ላይ በመሆኑ ነዋሪዎች አካባቢያቸው በዝንብ መወረሩን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል መንግሥት ባለበት አገር ትንሽ ለዓይን ያዝ ሲያደርግ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚዘረፉና ሥራ ላይ የሚያመሹ እናቶችና ልጃገረዶች፣ በስልክ ቤተሰብ ጠርተው ካልሆነ በስተቀር ብቻቸውን መግባት እንደማይችሉ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ለሚመለከተው ወረዳ ኃላፊዎችና ለፖሊስ ቢያመለክቱም፣ ያገኙት ምላሽ ‹‹ከአቅማችን በላይ ነው›› የሚል ስለሆነ፣ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ግራ መጋባታቸውን ገልጸው፣ ችግሩን ሊቀርፍላቸው የሚችል የመንግሥት አካል ካለ ጠይቀዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች ያነሱትን ሥጋትና ፍርኃት በሚመለከት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልደ ሩፋኤል ሐጎስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በቦታው ላይ የአካባቢው ነዋሪ መሆናቸውን የገለጹ ወጣቶች ተደራጅተው መምጣታቸውንና የመኪና ፓርኪንግ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነሱ ካስፈቀዱት ተግባር ውጪ ማዋላቸው ሲታወቅ ፈቃዳቸው ተሰርዞ አካባቢውን እንዲለቁ ሲጠየቁ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እንደገለጹና ሕገወጥ ድርጊቱን እንደቀጠሉ ገልጸዋል፡፡

ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ የክፍለ ከተማው ትራፊክ ፖሊስ ታርጋ በመፍታት እንዲያነሳ በደብዳቤ ቢያሳውቁም ተግባራዊ ሊሆን ባለመቻሉ፣ ለክፍለ ከተማና ለፖሊስ አካላት ጽፈው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን አቶ ወልደ ሩፋኤል አስረድተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...