የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድራቸውን መክፈል ላልቻሉና ሥራቸውን ላላቆሙ በዝናብ የሚለሙ እርሻዎች የብድር መክፈያ ጊዜ ማራዘሚያ አደረገ፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ናና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤያቸው፣ ‹‹በዝናብ የሚለሙ በባንኩ የብድር ድጋፍ የተቋቋሙ የእርሻ ፕሮጀክቶች በተለይም በማምረት ሒደት ላይ ያሉ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አሁን ብድራቸውን መክፈል የማይችሉ መሆኑ በባንኩ ባለሙያዎች ከተረጋገጠ፣ መሬቱ ጦም አድሮ በጥሻና በጫካ እንዳይሸፈን ከማድረግ አንፃር ሥራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ተለይተው ተጨማሪ ብድር እስካልጠየቁ ድረስ ወደ ፎርክሎዠር (ሐራጅ) ከመሄድ ይልቅ፣ በባንኩ የሪሃብሊቴሽን ሜካኒዝም ወለድ ካፒታላይዝ (Interest Capitalization) ተደርጎ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው እያሳሰብኩ፣ አፈጻጸሙን በተመለከተ በባንኩ ብድር የተቋቋሙ በዝናብ የሚለሙ ሰፋፊ እርሻዎች ግብረ ኃይል ክትትል እየተደረገ ሪፖርት እንዲያደርግ አስገነዝባለሁ፤›› ይላል፡፡
በዝናብ የሚያለሙ የትልልቅ እርሻዎች ባለቤቶች የብድር ይራዘምልን ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ ከዓመት በላይ ሆኗቸዋል፡፡