Sunday, September 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሸራር አዲስ ሆቴል

ተዛማጅ ፅሁፎች

የመኝታ፣ የሬስቶራንት እንዲሁም የመጠጥ አገልግሎት የሚሰጠው የሸራር አዲስ ሆቴል ባለቤት አቶ አምሐ ገብረ ጻድቅ ሰሞኑን ሆቴሉን ሲያስመርቁ እንደገለጹት፣ በቦሌ አካባቢ ጁፒተር ሆቴል አጠገብ የተገነባው ይህ ሆቴል ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ጠይቋል፡፡ ከአራት ዓመታት በላይ የግንባታ ጊዜ የወሰደው የሆቴሉ 30 ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ ሙሉ ለሙሉ ሥራ ሲጀምር ለ70 ሰዎች የሥራ ዕድል ያስገኛል ብለዋል፡፡ በሆቴሉ ሕንፃ አናት ላይ ያለውን መመገቢያ ጨምሮ፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የጃኩዚ፣ የጂምና ሌሎችም አገልግሎት መስጫዎች እንዳሉት ታውቋል፡፡ የሆቴሉ ባለንብረቶች በሆቴል ሥራ መስክ የቆየ ልምድ ያላቸው፣ በደርግ መንግሥት ወቅት አፍሪካ ሆቴል ይባል የነበረውና በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ካፌ በሚል ስያሜ ፒያሳ አካባቢ አገልግሎት የሚሰጠውን ካፍቴሪያ ያስተዳድራሉ፡፡ በአዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት በየወሩ ሁለት ሆቴሎች በአማካይ ወደ ሥራ እየገቡ እንደሚገኙ መረጃዎች ሲያመላክቱ፣ በተለይ ቦሌ የሆቴሎች መናኸሪያ እስክትመስል ድረስ በየመንገዱ ዳርቻና ውስጣ ውስጡን በርካታ ሆቴሎች ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡ በግንባታ ላይ የሚገኙ የአገር ውስጥና የውጭ ሆቴሎችም ሥራ ለመጀመር ዳር ዳር ይላሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች