Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመት 39.4 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱን አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

– 6.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም ገልጿል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ፣ በብድርና ቦንድ ሽያጭ ከ39.4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመስጠት የግማሽ ዓመት ዕቅዱን ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማኔጅመንት ከጥር 19 እስከ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ኃይሌ ሪዞርት ባካሄደው ስብሰባ ማረጋገጥ የቻለው፣ ባንኩ ከተቀማጭ ገንዘብና ከብድር የተገኘውን ገንዘብ መልሶ ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በብድርና በቦንድ ሽያጭ መልክ ማቅረብ መሆኑንና ይህንን አሠራሩን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን፣ ባንኩ ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ያወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡

ባንኩ በግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ ወደ አገር ውስጥ ከተላከ የሐዋላ ገንዘብ 2.06 ቢሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ከወጪ ንግድ 292.1 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ገልጿል፡፡

ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ በሩብ ዓመቱ 330.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቁሞ፣ ከታክስ በፊት 12.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንና የግማሽ ዓመት ትርፉም 6.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጿል፡፡ በግማሽ ዓመቱ 18.4 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉንና ካለፈው በጀት ዓመት ከነበረው 247 ቢሊዮን ብር ወደ 260.2 ቢሊዮን ብር ሊያሳድግ እንደቻለ አክሏል፡፡

ባንኩ በአሁኑ ጊዜ 1,000 ቅርንጫፎች በመክፈት ተደራሽነቱን እያሰፋ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በግማሽ ዓመቱ 1.2 ሚሊዮን አዲስ ሒሳቦችን በመክፈት፣ የባንኩን የተቀማጭ ሒሳቦች ብዛት 11.9 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን አመልክቷል፡፡ በመረጃ መረብ (ቲ-24 ኮር ባንኪንግ ሶሉዩሽን) የባንካቹን 916 ቅርንጫፎች ማገናኘት መቻሉን መግለጫው ጠቁሟል፡፡ በስድስት ወራት ውስጥ የኤቲኤምና የፖስ ማሽኖችን በመጠቀም የክፍያ ሥርዓቱን ለማዘመን እየሠራ መሆኑን የገለጸው መግለጫው፣ 624,769 ካርዶችን ለደንበኞች ማሠራጨቱን፣ 305,365 ደንበኞች የሞባይል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውንና 14,009 የኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንዳሉትም አብራርቷል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች