- ½ ኪሎ ደበርጃን
- ¼ ኪሎ ፔፐሮኒ
- 1 በክብ ቅርፅ የተመተረ ቀይ ሽንኩርት
- 3 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
- ½ ኩባያ የተከተፈ ፐርሰሜሎ
- ¼ ኪሎ ቲማቲም
- ¼ ኩባያ የሚነሰነስ ፐርሰሜሎ
- ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ
- ዘይት፣ ለመጥበሻ
አሠራር
- ደበርጃን በስሎ መትሮ ጨው በገባበት ውኃ ውስጥ ለግማሽ ሰዓት መዘፍዘፍ፡፡
- በንፁህ ጨርቅ አድርቆ በፈላ ዘይት ውስጥ መጥበስ፡፡
- ፔፐሮኒውን በቁመት መትሮ ውኃውን አጥልሎ በጨርቅ ላይ ከደረቀ በኋላ በዘይት መጥበስ፡፡
- ለመጥበሻ ከዋለው ግማሽ ኩባያ ዘይት ድስት ውስጥ ጨምሮ ነጭና ቀይ ሽንኩርት እንዲሁም ፐርሰሜሎ ቀላቅሎ መጥበስ፡፡
- በሌላ ድስት ውስጥ ከደበርጃኑ ትንሽ ከፔፐሮኒው ትንሽ ከሥር አንጥፎ እላዩ ላይ የተጠበሰውን ሽንኩርት መጨመር፡፡ አስፈላጊ ከሆነም በክቡ የተመተረ ወይም የተፈጨ ቲማቲም ማድረግ፡፡ የቀረውን ደበርጃንና ፑ
- ፔፐሮኒ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ ፐርሰሜሎ እላዩ ላይ መነስነስ፡፡ በክብ የተመተረ ቲማቲም እላዩ ላይ በመደርደር ትንሽ ዘይት አፍስሶ ምድጃ ውስጥ ወይም በፎርኒሎ ማብሰል፡፡
አራት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)