ሱ ሼፍ ጌታዋ በሪሁን
ጥሬ ዕቃዎች
- ½ ኪሎ ተልጦና ተቀቅሎ የተፈጨ ድንች
- 2 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቂቤ
- 1 ብርጭቆ ወተት
- ½ የሻይ ማንኪያ ጨው
- ¼ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- ¼ የሻይ ማንኪያ ለውዝ
አዘገጃጀት
- በመካከለኛ ድስት ውስጥ ቅቤውን በመጨመር ከቀለጠ በኋላ የተፈጨውን ድንች መጨመር ከሁለት ደቂቃ በኋላ ወተት፣ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ለውዙን በመጨመር ለአምስት ደቂቃ ማማሰል፡፡
- በመጨረሻም በተዘጋጀው ሳህን ላይ በማድረግ መመገብ