Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍር​‹‹ምርጫው ፈፅሞ ነፃና ፍትሐዊ የመሆን ዕድል የለውም››

​‹‹ምርጫው ፈፅሞ ነፃና ፍትሐዊ የመሆን ዕድል የለውም››

ቀን:

የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ዋነኛ ተፎካካሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ኪዛ ቤሲጊዬ፣ በዚህ ሳምንት በሚደረገው ምርጫ ተስፋ መቁረጣቸውን ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ደጋፊ የሆኑት ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች የተለመደውን አፈና በደጋፊዎቻቸው ላይ እያካሄዱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በምርጫ ዘመቻቸው ላይ አሻጥር እየፈጸሙ ነው ብለዋል፡፡ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጪስ በመጠቀም ደጋፊዎቻቸውን መበተናቸውን፣ አንድ ሰው ገድለው 19 ያህሉን ማቁሰላቸውን ተናግረዋል፡፡ እሳቸውንም ለአጭር ጊዜ እንዳሰሯቸው አክለዋል፡፡ ፖሊስ ደግሞ የተቃዋሚው መሪ ደጋፊዎች ዘረፋና ንብረት ማውደም ውስጥ ተሰማርተዋል ይላል፡፡ ከ71 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ጋር ከዚህ በፊት ሦስቴ ተወዳድረው የተሸነፉት ቤሲጊዬ፣ አሁንም መታገሉን እንደሚቀጥሉ ተናግረው አፈናውና ውክቢያው የኡጋንዳ ምርጫን እያበላሸው ነው ብለዋል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት ኪዛ ቢሲጊዬ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...