Wednesday, February 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​የማንቂያ ደወል!

​የማንቂያ ደወል!

ቀን:

አንድ መምህር የሀምሳ ብር ኖት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በመያዝ ለተማሪዎቹ ‹‹ማን ነው ይህን የሚፈልግ›› አላቸው። ሁሉም እጃቸው በማውጣት ‹‹ቲቸር እኔ… እኔ …›› ማለት ጀመሩ።

መምህሩ ብሯን በእጁ ጭምድድ ካደረጋት በኋላ ዳግም ወደላይ ከፍ
አድርጎ ‹‹አሁንስ ማነው መውሰድ የሚፈልግ?›› አላቸው።

ሁሉም ተማሪዎች አሁንም እጃቸውን በማውጣት ልክ እንደመጀመሪያው
‹‹እኔ… እኔ›› እያሉ ጩኸታቸውን ቀጠሉ።

መምህሩ ብሯን መሬት ላይ ከጣላት በኋላ በጫማው እየረጋገጠ አቆሸሻት። ከዚያ ወደ
ላይ ከፍ በማድረግ ‹‹አሁንስ ማነው መውሰድ የሚፈልግ?›› አላቸው።

ተማሪዎቹ ብሯን በዋዛ ሊያሳልፏት ስላልፈለጉ ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ ጊዜያት እጆቻቸውን በማውለብለብ ቲቸር ‹‹እኔ… እኔ…›› ማለታቸውን ቀጠሉ።

መምህሩ ብሯን ወደ ኪሱ በመመለስ ‹‹የዛሬው ትምህርታችሁ እዚህ ላይ ያበቃል። ቀዳደህ ካልጣልካት በስተቀር በማሸት፣ በማቆሸሽና በመረጋገጥ የዚህችን ወረቀት ዋጋ መቀነስ
እንደማይቻለው ሁሉ እናንተንም ሰዎች ሊያንቋሽሿችሁ፣ ሊያሳንሷችሁ፣ ሊያዋርዷችሁ፣ ሊያፌዙባችሁ፣ … ጥረት ቢያደርጉም ትክክለኛ ዋጋችሁን ሊቀንሱ እንደማይችሉ እወቁ።

/መምህሩ ትንሽ ፋታ ከወሰደ በኋላ… /

ይህን ካወቃችሁ ከውድቀት በኋላም መነሳት ትችላላችሁ። ሁሉም ትክክለኛ ዋጋችሁን እንዲያውቅ ማድረግ ትችላላችሁ። ነገር ግን ትክክለኛ ዋጋችሁን የረሳችሁ እና በራስ መተማመናችሁን ያጣችሁ ቀን ሁሉንም ነገር ማጣታችሁን እወቁ!››

የማንቂያ ደወል፤ የትምህርት ቤቱ ደወል ተደወለ፡፡ መምህሩም ከክፍል ወጣ፡፡

  • ጌጡ ተመስገን በገጹ እንደከተበው

 

*******

የምስክርነት ቃል

ሙላህ ለምስክርነት ቀርቦ ነው፡፡ ዳኛው ሙላህን

“ሰውዬው ሲገድል ተኩሱን በትክክል አይተሀል?” አሉት፡፡

ነስሩ “ድምፁን ሰምቻለሁ” አለ፡፡

“በቃ መረጃህ በቂ አይደለም” አሉ ዳኛው ቀና ብለው፡፡

ነስሩ ከዳኛው ጀርባ አሻግሮ ሲያይ ምን እንደሚያይ ግራ ገብቷቸው ወደ ኋላቸው ሲዞሩ፣ ነስሩ ከት ብሎ ይስቃል፡፡

ዳኛው ተናደው “ችሎት ስለተዳፈርክ ቅጣት ይጠብቅሀል” አሉት፡፡

“ምን አድርጌ?” አለ ነስሩ

“ችሎት ፊት ካለአግባብ ስቀሀል”

“እርሶ እኔ ስስቅ አይተውኛል?”

“ድምፅህን ሰምቻለሁ” አሉት

“የርሶም መረጃ በቂ አይደለም” ብሎ እርፍ፡፡

  • መሃመድ ጣፋ “ነስሩዲን እና ቀልዶቹ” (1998)

 

*******

ቫላንታይን ዴይን ማክበር በኢራን ወንጀል ሆነ

ከቫላንታይን ዴይ እሑድ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም. (ፌብሬዋሪ 14 ቀን 2016) ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ዓርብ ዕለት የኢራን ፖሊስ ቫላንታይን ቀን ለማክበር ዝግጅቶችን ማድረግ እንደጥፋት እንደሚቆጠር ማስታወቁን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር፡፡ እንደ አበባ መደብርና ሌሎችም ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ነገሮችን የሚሸጡ ንግድ ቤቶችን ፖሊስ አስጠንቅቋል፡፡ በቫላንታይን ዴይ ቀን ስም የሚዘጋጁ ማንኛውም ዓይነት ፕሮግራሞች ስጦታ መለዋወጥም ሕገወጥ ነው ተብሏል፡፡ የዚህ መነሻው በአገሪቱ የምዕራቡ ዓለምን ባህል መስረጽን መከላከል ነው፡፡ እንደ ሳውዲ ዓረቢያ ያሉ አገሮችም ተመሳሳይ አቋም ሲኖራቸው እንደ ዱባይ ባሉት ደግሞ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ቀኑ፡፡

*******

ቤተ ክርስቲያኗ ያለባትን የገንዘብ ዕዳ በጸሎት ልትከፍል ነው

በሩሲያ አንድ ክልል ውስጥ የምትገኝ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ኩባንያ ያለባትን 3244 ዶላር ዕዳ እንዲሁም በፍርድ ቤት የተጣለባትን የ817 ዶላር ቅጣት ከገንዘብ ይልቅ በጸሎት እንድትከፍል ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ እንደ ዘገባው ቤተ ክርስቲያኗ ለኩባንያው ጤንነት በመፀለይ ዕዳዋን ታወራርዳለች፡፡ ዘገባው እንደሚያመለክተው ቤተ ክርስቲያኗ መጀመሪያ ካለባት ዕዳ ለኩባንያው የተወሰነውን ከፍላለች፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...