በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተሠራውና ‹‹ዕንቁላል ቤት›› በመባል የሚታወቀው የንጉሠ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት በግቢ ገብርኤልና በፊት በር መካከል ይገኛል፡፡ ዕንቁላል ቤት ‹‹ታላቁ ቤተ መንግሥት›› እንዲሁም ‹‹ዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት›› በመባል በሚታወቀው ቅጥር ግቢ ከበዓታ ለማርያም ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ የቀድሞዎቹ መሪዎች የደርጉ ሊቀመንበር በኋላ የኢሕዲሪ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ በኋላ የሽግግሩ መንግሥት ፕሬዚዳንት በመቀጠልም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መኖሪያቸው በግቢ ውስጥ የነበረ በመሆኑ፣ አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በመኖሪያነት በመቀጠላቸው ዕንቁላል ቤቱ ለጎብኚዎች ክፍት አልሆነም፡፡
(ሔኖክ መደብር)