Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​ትምህርት ሚኒስቴር ከቻይና ኢንስፑር ግሩፕ ጋር የ20 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ

​ትምህርት ሚኒስቴር ከቻይና ኢንስፑር ግሩፕ ጋር የ20 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ

ቀን:

በ300 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በአሥር ዩኒቨርሲቲዎች ተፈጻሚ የሚሆን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የ20 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት፣ በትምህርት ሚኒስቴርና በቻይናው ኢንስፑር ግሩፕ ኩባንያ መካከል ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ የፈረሙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጥላዬ ጌጤና የኢንስፑር ግሩፕ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪቻርድ ዋንግ ናቸው፡፡

ድርጅቱና ትምህርት ሚኒስቴር ስምምነቱን የፈረሙት የካቲት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱን የሚያስተዳድረው የዓለም ባንክ ለፕሮጀክቱ ይሁንታውን የሰጠው በጥቅምት ወር እንደነበር በፊርማው ሥነ ሥርዓት ወቅት ተገልጿል፡፡

ለዚህም መዘግየት ዋነኛው ምክንያት ከተጫራቾቹ መካከል አንዱ የሆነው ሌላው የቻይና ኩባንያ ሁዋዌ በጨረታው ግልጽነት ላይ ጥያቄ በማንሳቱ፣ የተነሳውን ጥያቄ ለማጣራት ጊዜ በመፍጀቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሁዋዌ ያቀረበው ቅሬታ አሸናፊው ድርጅት ከዚህ በፊት የተሳተፍኩባቸው አገሮች በማለት የዘረዘራቸው አገሮች ውስጥ ያከናወነው ተግባር እንደሌለ የሚገልጽ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም በቬኒዙዌላ፣ በታንዛንያ፣ በኬንያና በቻይና በተመሳሳይ የሥራ መስክ ተሳትፌያለሁ በማለት ያቀረበው ማስረጃ ውድቅ እንዲሆን የሚጠይቅ ነበር፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ታደሰ መረሳ በበኩላቸው፣ በዚህ ዓይነቱ አስተያየት አይስማሙም፡፡ ‹‹ከመጀመሪያው ጀምሮ የግዥ ሒደቱ በግልጽና ያለምንም አድልዎ እንዲከናወን የቴክኒክ ግምገማው የተሠራው ከእኛ ውጪ በሆኑና ልምድ አላቸው በሚባሉ የመረጃና መረብ ደኅንነት ባለሙያዎች አማካይነት ነው፤›› በማለት የግምገማውን ሒደት ከችግር የፀዳ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ ይህ ቢሆንም ግን ከሁዋዌ በኩል ጥያቄ መቅረቡን ገልጸው፣ ‹‹የቀረቡትን ጥያቄዎች ለማጣራትና ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚል ከዓለም ባንክ በጥቅምት ወር ይሁንታ ላገኘ ፕሮጀክት ዛሬ ተፈራርመናል፤›› ብለዋል፡፡

በዚህም ጥቆማውን በተለያዩ ደረጃዎች እንዳጣሩ የሚገልጹት ሚኒስትር ዴኤታው ደግሞ፣ ‹‹በተለያዩ ደረጃዎች የማጣራት ሥራ ስናከናውን ቆይተናል፡፡ ከእኛም አልፎ ሚኒስትሩ በተገኙበት በግዢው ላይ ያሉ አካላት በሙሉ የተሳተፉበት ስብሰባ አድርገን ጉዳዩን ለማጣራት ሞክረናል፡፡ ይህን ሁሉ አድርገን ጨረታውን ሊያሰርዝ የሚችል ምንም ዓይነት ምክንያት አላገኘንም፤›› ሲሉ በፊርማው ሥነ ሥርዓት ወቅት አስረድተዋል፡፡

ይህ በ18 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ፕሮጀክት ትምህርት ቤቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ በመንግሥት እየተተገበረ የሚገኝ ፕሮጀክት እንደሆነ ያስረዱት ደግሞ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ዶ/ር ገበየሁ ወርቅነህ ናቸው፡፡

በጨረታው ወቅት የተሳተፉት ኩባንያዎች ሦስቱ ከቻይና ሲሆኑ፣ አንደኛው ደግሞ የጀርመን ኩባንያ ነው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...