Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበትግራይ ክልል ወደ ሌላ ወረዳ የተጠቃለሉ የእምባሰነይቲ 17 ቀበሌዎች ተቃውሞ አሰሙ

በትግራይ ክልል ወደ ሌላ ወረዳ የተጠቃለሉ የእምባሰነይቲ 17 ቀበሌዎች ተቃውሞ አሰሙ

ቀን:

  • ‹‹ሕወሓት ክህደት ፈጽሞብናል›› ነዋሪዎቹ

በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የቀድሞ የእምባሰነይቲ ወረዳ በሁለት ወረዳዎች እንዲጠቃለሉ የተደረጉ የ17 ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ ወረዳቸው እንዲመለስላቸው ከሃያ ዓመት በፊት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ተቃውሞ አሰሙ፡፡

የክልሉ መንግሥት በ1988 ዓ.ም. 84 የነበሩትን የክልሉ ወረዳዎች በአቅምና በጀት እጥረት ምክንያት ወደ 34 ዝቅ ያደረገ ሲሆን፣ በተለያዩ አካባቢዎች ፈርሰው ወደ ሌላ ወረዳ እንዲሸጋሸጉ የተደረጉ ወረዳዎች ተቃውሞ ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል የአዲሱን የወረዳ አወቃቀር ያልተቀበሉ ቀደም ሲል በማዕከላዊ ዞን በ‹‹እምባሰነይቲ ወረዳ›› ሥር የነበሩት 17 ቀበሌዎች ላለፉት 20 ዓመታት ተቃውሞ ሲያሰሙ የቆዩ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ያስከተለ ጉዳይ እየሆነ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ቀበሌዎቹ ወደ ወረዒለኸ ወረዳ እንዲጠቃለሉ የተደረጉ ሲሆን፣ በተለይ አንዳንድ የቀበሌ ነዋሪዎች ፍትሕ ፍለጋና ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች እስከ 52 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚገደዱ የአካባቢው ምንጮች ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በመልካም አስተዳደር ዕጦት ላይ እየተደረጉ ባሉ ሕዝባዊ ኮንፈረንሶች የሕዝቡ ተቃውሞ አይሎ የወጣ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በሕዝቡ የተወከሉት ግለሰቦች ወደ ፌዴራል መንግሥትና ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አቤቱታቸውን ይዘው አዲስ አበባ ድረስ መምጣታቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የወረዳዎች አወቃቀር በክልሉ በጉልህ የሚታይ አለመግባባትና ቅሬታ የፈጠረ በመሆኑ፣ የእነዚህ ቀበሌዎች አቤቱታ ግን ባለፈው ዓመት በ12ኛ የሕወሓት ጉባዔ በአጀንዳነት ተነስቶ እንዲጠናና እንዲጠራ በሚል ታልፎ ነበር፡፡

አሁንም ድረስ ዕልባት ሳያገኝ የዘለቀው ይኼው አለመግባባት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የሪፖርተር ምንጮች ያረጋገጡ ሲሆን፣ ‹‹ፍትሕ ርቆናል፤ መንግሥት የለንም፣ ከርቀት የተነሳ ጉዳያችንን ትተናል፤›› ወዘተ የሚሉ ቅሬታዎች በኮንፈረንሱ ማንሳታቸውንም አክለዋል፡፡

በፍትሕ ዕጦት ምክንያት ሕዝቡ እያለቀሰ መሆኑንና በዚህ ሳቢያ ሽፍታና ዘራፊ በአካባቢው መበራከቱም በስብሰባው መነሳቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የእምባሰነይቲ አካባቢ ከመነሻው ጀምሮ በደርግ አስተዳደር ሥር ያልወደቀ ‹‹ሐራ መሬት›› በመባል ከሚታወቁ ለትጥቅ ትግሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ አካባቢ መሆኑን የድርጅቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ‹‹የታገልንበት ዓላማ ፍትሕና መልካም አስተዳደር ለማግኘት ነበር፡፡ የእናንተ ባሰብን፡፡ ውድብ [ሕወሓት] ክህደት ፈጽሞብናል፡፡ ጥያቄችን የማይመልስልን ከሆነ በቃ ተለያይተናል፣ አያስተዳድረንም፤›› የሚሉ አስተያየቶች መሰማታቸው ተጠቁሟል፡፡

ጥያቄው አሁን ያገረሸበት ምክንያት የፍትሕ ማጣትና የፀጥታ መደፍረስ ያስነሳው ሲሆን፣ የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሚካኤል አብረሃ፣ ‹‹ጥያቄው የጥቂት ሰዎች ቅሬታ ነው፡፡ ዕርምጃ እንወስዳለን፣ ቀስቃሾችን እናስራለን፤›› የሚል ምላሽ በመስጠታቸው በስብሰባው የተገኘውን ሕዝብ ለተቃውሞ እንደጋበዘና መበተኑን ስብሰባውን የታደሙ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ከድርጅቱ የተወከሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልም፣ ‹‹የደርግ ናፋቂዎች›› በማለት ምላሽ በመስጠታቸው ምክንያት ሕዝቡን ወደ አላስፈላጊ ተቃውሞ አነሳስተውት የነበረ መሆኑን፣ ‹‹ደርግ ከናፈቀን ከደርግ በላይ ብሳችኋል ማለት ነው፤›› የሚል ምላሽ ከሕዝቡ መሰማቱም ተገልጿል፡፡  

በስብሰባው ከተገኙት መካከል የወረዳው የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ አቶ አረጋይ ገብረ ማርያም፣ በ1988 ዓ.ም. የወረዳዎች ሽግሽግ የተደረገው በአቅም ማነስና ልማትን ለማስተሳሰር ያለመ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸው፣ የእምባሰነይቲ ነዋሪዎች የዚህ ሽግሽግ ተቃውሞ የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሕዝቡ ተቃውሞ እየተባባሰ መምጣቱንና በሕዝባዊ ኮንፈረንሱ የተፈጠረውን አለመግባባት ያልካዱት አቶ አረጋይ፣ ‹‹የአካባቢው አስተዳደርም ሆነ የክልሉ መንግሥት ሊመልሰው የማይችል ጥያቄ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው፣ ‹‹የእምባሰነይቲ ሕዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል፡፡ ይህንን የሕዝብ ጥያቄ መመለስ ከጀመርን ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች በክልሉ ይቀጥላሉ፡፡ የልማት ሥራዎች መሥራት አይቻልም፡፡ ቅሬታ ስንሰማ ልንውል ነው ማለት ነው?›› ብለዋል፡፡

ተቃውሞውን እየገለጸ ያለው ሕዝብ ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ወረዳው በድጋሚ እንዲዋቀር ሲደረግ ለአምስት ዓመት ብቻ ነው ተብሎ እንደነበር፣ እንዲሁም በ1996 ዓ.ም. በተነሳ ተቃውሞ ሕዝቡ ሠልፍ ወጥቶ የነበለት ሐውዜን መንገድን ዘግቶ እንደነበር፣ በርካቶችም ለእስራትና ለድብደባ መዳረጋቸው ይነገራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...