Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

  የሳምንቱ ገጠመኝ

  ቀን:

  ረፋድ ላይ ከቤቴ ወጥቼ ትራንስፖርት ሳጣ ‹ልወዝወዘው በእግሬ› ብዬ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ እንደ እኔ ቆሞ ታክሲ መጠበቅ የሰለቻቸው ወገኖቼ የመንገዱን ግራና ቀኝ ይዘው ወሬያቸውን እየሰለቁ ይጓዛሉ፡፡ ከፊቴ ሁለት ወጣት ሴቶች በቫላንታይንስ ቀን የገጠማቸውን ነገር እያነሱ በሳቅ ይፍለቀለቃሉ፡፡ አንዷ፣ ‹‹የፍቅረኞች ቀን ከሚሉት የወፈፌዎች ቀን ቢሉት ይሻላል፡፡ እንደዚያ ቀይ ቀለም የተደፋባቸው መስለው በየአጥሩና በየግንቡ ሥር ሲላላሱ …›› እያለች ስትስቅ፣ ‹‹አንቺ እሱ ይገርምሻል ያቺ … እና ጓደኛዋን በነጋታው ጠዋት ብታያቸው እኮ ኩሽና ውስጥ ያደሩ ይመስሉ ነበር …›› ብላት ዞር ስትል እኔ ከኋላ አለሁ፡፡

  ሁለቱም እንደማፈር ብለው ከእኔ በተቃራኒ ባለው የመንገድ ጠርዝ አቅጣጫ ቀይረው ቆም አሉ፡፡ የሚያወሩትን እንድሰማባቸው እንዳልፈለጉ ስለገባኝ እኔም በተወራው እየተገረምኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ በእርግጥ የፍቅረኞች ቀን ተብሎ ባለፈው ሳምንት እሑድ የነበረውን ቅጥ አምባሩ የጠፋበት ተውኔት በየፈርጁ እኔም አይቻለሁ፡፡ ከቦሌ ትምህርት ቤት ወደ ሃያ ሁለት የሚያመራው አካባቢ በምሽት ይታይ የነበረው ነገር በጣም ያስጠላል፡፡ ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ ታዳጊ ሴቶች ሳይቀሩ ቀይ አጭር ቀሚስ ከአላባሽ ጋር ለብሰውና በስካር እንዳይሆኑ ሆነው ለተመለከተ፣ ይህቺ አገር ተረግማለች ወይ ያሰኘው ነበር፡፡ የእኔ ጉዳይ ከዚህ በኋላ ይቀጥላል፡፡

  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚያመራውን ታክሲ ተሳፍሬ ጉዞው ከመጀመሩ አንድ ተሳፋሪና ወያላ ጠብ ጀምረዋል፡፡ ተሳፋሪው በሞባይል ስልኩ ላይ ያስጫነውን ሙዚቃ ድምፅ ከፍ አድርጎ ከፍቶታል፡፡ አጠገቡ ያሉትም ሆኑ ሌሎች ተሳፋሪዎች ዝም ብለዋል፡፡ ወያላው ግን፣ ‹‹ወንድም የጆሮ ማዳመጪያህን በመጠቀም ሙዚቃህን ስማ፡፡ የእኔንም ሆነ የሌሎችን ተሳፋሪዎች መብት አክብር …›› ይለዋል፡፡ ተሳፋሪው፣ ‹‹የአማርኛ ዘፈን ቢሆን ኖሮ ምንም አትልም ነበር፡፡ የብሔሬን ሙዚቃ በመናቅህ ነው እንዲህ የምትንጨረጨረው …›› እያለ ሲውረገረግ እኔ በበኩሌ በጣም ደነገጥኩ፡፡

  ይኼን ጊዜ ሌሎችም በድንጋጤ ተናጋሪውን በተረበሸ ስሜት ማየት ጀመሩ፡፡ ወያላው በንዴት ጦፎ፣ ‹‹ስማ አንተ እዚያው በጠበልህ፡፡ እኔን ብሔር ምናምን እያልክ አታነካ7ካኝ፡፡ ይኼንን ቆሻሻና የወረደ ንግግርህን አርም፡፡ አለበለዚያ ታክሲውን አስቁሜ ትወርዳለህ፡፡ አሁንም በጆሮ ማዳመጫ የማታዳምጥ ከሆነ ትወርዳለህ፤›› ብሎ አፈጠጠ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ነገር ለማብረድ ‹አንተም ተው፣ አንተም ተው…› ማለት ቢጀምሩም፣ ተሳፋሪው ሙዚቃውን ዘግቶ ቡጢ ለመሰንዘር ተዘጋጀ፡፡ ወያላው ተንደርድሮ ሲመጣ ትርምስ ተጀመረ፡፡ ሾፌሩ ታክሲውን ጥግ አስይዞ አቆመ፡፡

  ወያላው ከወንበር ሥር ሌባ ጎማ ይዞ ወርዶ፣ ‹‹ና ይለይልን …›› እያለ ሲፎክር ተሳፋሪው፣ ‹‹ምን ታመጣለህ …›› በማለት ሲያቅራራ ሰዎች መሀል ገብተው ለያዩዋቸው፡፡ በብልግና የታጀቡ ስድቦችንና እርግማኖችን እስኪበቃን ከሰማን በኋላ ጉዞ ልንጀምር ስንል፣ ወያላውና ሾፌሩ ተሳፋሪውን አንጭንም አሉ፡፡ ተሳፋሪው ደግሞ፣ ‹‹መብቴን ማንም አይቀማኝም …›› ብሎ ተንደርድሮ ገብቶ ወንበሩን ያዘ፡፡ ይኼኔ ወያላው ድንገት በያዘው ሌባ ጎማ ሲነዝር ለጥቂት ሳተው፡፡ የባሰ ትርምስ ተፈጠረ፡፡ በአካባቢው ጥበቃ የሚያደርጉ ፖሊሶች ወይም የትራፊክ ፖሊሶች ባለመኖራቸው፣ ደም ለመቃባት የፈለጉትን ሁለቱን ሰዎች መገላገል የእኛ ሥራ ሆነ፡፡ ወያላው ተው ሲባል ተሳፋሪው፣ ተሳፋሪው ተው ሲባል ወያላው እየባሱ መከራ አየን፡፡

  በስንት ማባበልና ልመና ተሳፋሪው በሌላ ታክሲ እንዲሸኝ ተደርጎ ለበርካታ ደቂቃዎች የተቋረጠው ጉዞ እንደገና ቀጠለ፡፡ ሁሉም የመሰለውን እያነሳ ሲያወራ እኔ ግን አንድ ነገር ቆረቆረኝ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ አስቸጋሪ የሆነው? ለራሳችን የማንፈልገውን ሌሎች ላይ ለምንድነው የምንጭነው? የሆነ ነገራችን ሲነካ ለምን ከብሔር ጋር እናገናኛለን? ችግር ሲያጋጥም መቻቻል አቅቶን ምንድነው የሚያባላን? እስኪ ፌስቡክን ተመልክቱ፡፡ በአገር ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ ውይይቶች መቋጫቸው ስድብ ነው፡፡ ዘለፋ ነው፡፡ ጥላቻ ነው፡፡ በመረጃ ላይ ያልተመሠረቱ የወሬ ጫፎችን ይዞ መባላት፣ ትልቅ አገርና ማንነት እያለን ወንዝ የማያሻግር ዘርና ጎሳ ላይ መጣድ፣ በሐሰተኛ የታሪክ ግምገማ የሌለ ነገር ማውራት፣ ወዘተ ምን ያደርግልናል? ይህንን ገጠመኜን ያጫወትኳቸው አንድ የታወቁ ምሁር እንዲህ አሉኝ፡፡

  ‹‹ከሌሎች አገሮች የተሻለ ታሪክና አኩሪ አገር እያለን እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ እየሆንን ነው፡፡ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ በፖለቲካና በመሳሰሉት አመለካከቶች ልዩነት እንዳለ እየታወቀ፣ ልዩነትን ለማስተናገድ አለመፈለግ በብዛት ይታያል፡፡ አንድ ሰው የመሰለውን ሲናገር በመንጋ ተነስቶ ማውገዝ በርትቷል፡፡ የራስን ማንነት በድፍረት ሳይገልጹ በፌስቡክ የዋሆችን የማስፈጀት ዘመቻ ተበራክቷል፡፡ በየቦታው ወሬ ከመድራቱ የተነሳ የተማረውም ያልተማረውም ሐሜተኛና አሉባልተኛ ሆኗል፡፡ በዚህ መሀል የዋሆች እውነት እየመሰላቸው ይማገዳሉ፡፡ የራሳችንን ተምሳሌታዊ የሆኑ መልካም እሴቶችን ንደን፣ የባዕዳኑን የባህል ወረራ በተበላሸ ገጽታው ተቀብለን፣ ከዓለም ጋር እኩል መራመድ አቅቶን እያነከስን ነው፡፡ በየቀኑ የምንሰማቸው ነገሮች በሙሉ በሐሰት የተጀቦኑ ናቸው፡፡ አገር በውሸት የሚያድግ ይመስል ሁሉም የሐሰት ወሬ ላይ ተጥዷል፡፡ ወሬ ዕውቀት አይደለም፡፡ ወሬ የሚያስንቅ ወረርሽኝ በሽታ ስለሆነ ወደ ቀልባችን እንመለስ፤›› ነበር ያሉት፡፡

  (ቁምነገር ካሳ፣ ከሰሚት)

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...