Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​የአያት አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ተፈቱ

​የአያት አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ተፈቱ

ቀን:

በሪል ስቴት ልማት ፈር ቀዳጅ የሆነው አያት አክሲዮን ማኅበር ከፍተኛ ባለድርሻና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ፣ ከስድስት ዓመታት እስራት በኋላ ባለፈው ዓርብ የካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ተፈትተው ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ሊፈቱ የቻሉት ተመሥርቶባው ከነበረው የአራጣ ማበደር ወንጀል ጥር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በነፃ በመሰናበታቸው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ በነበሩትና በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ በተመሠረተባቸው አቶ መርክነህ ዓለማየሁና ባልደረቦቻቸው፣ 23 ክሶች ተመሥርቶባው ላለፉት ስድስት ዓመታት በእስር ላይ ሆነው ሲከራከሩ የቆዩት አቶ አያሌው ተሰማ፣ ዶ/ር መሐሪ መኮንንና አቶ ጌታቸው አጎናፍር መሆናቸው ይታወሳል፡፡

አያት አክሲዮን ማኅበር፣ አቶ አያሌውና አብረዋቸው የተከሰሱት ግለሰቦች በባለሥልጣኑ ዓቃቤ ክስ የተመሠረተባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት ነበር፡፡ ክሱም ቤት በዱቤ በመሸጥ የባንክ ሥራ ተክቶ መሥራት፣ በዱቤ ለተሸጡ ቤቶች ቫት ከራሳቸው ባለመክፈል ለገዥዎች ማስተላለፍ፣ ሐሰተኛ ሰነድ ማቅረብ፣ ያለቫት ደረሰኝ ግብይት መፈጸም፣ ወጪን በማናር የገቢ ግብር መሰወር፣ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን ለሦስተኛ አካል አሳልፎ መስጠት፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና የውጭ አገር ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ይዞ መገኘት የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ክሶች ነበሩ፡፡

ክሱን የመረመረው የሥር ፍርድ ቤት ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም. አክሲዮን ማኅበሩንና ግለሰቦቹን በ21 ክሶች ጥፋተኛ በማለት አቶ አያሌውን በ12 ዓመታት ጽኑ እስራትና ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት፣ ዶ/ር መሐሪን በ12 ዓመታት ጽኑ እስራትና 436 ሺሕ ብር ቅጣት፣ አቶ ጌታቸውን በአሥር ዓመታት ጽኑ እስራትና ከ400 ሺሕ ብር በላይ ቅጣት ወስኖባቸው ነበር፡፡ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ፍርድ ቤት ይግባኝ ያሉት እነ አቶ አያሌው፣ ከሁለት ዓመታት በላይ በቆየ የይግባኝ አቤቱታ ጥር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ውሳኔ ከአራጣ ማበደር ክስ ነፃ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአክሲዮን ትርፍ በመውሰዳቸው ብቻ ብድር ሳይኖር አራጣ አበድረዋል ሊባሉ እንደማይገባ፣ ሌሎች ባለድርሻዎችም ድርሻቸውን ወስደው ሳለ አራጣ አበድረዋል መባል እንደማይገባ በመግለጽ ክሱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ በርካታ ክሶችንም ውድቅ አድርጓቸዋል፡፡ በአጠቃላይ አያት አክሲዮን ማኅበሩ ተወስኖበት የነበረው ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ መቀጮ ተሰርዞለት፣ ጥፋተኛ በተባለባቸው ሦስት ክሶች በእያንዳንዳቸው 500 ሺሕ ብር በድምሩ 1.5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ተወስኖለታል፡፡

አቶ አያሌው የገንዘብ ቅጣቱ ቀርቶላቸው በስምንት ዓመታት እስራት፣ አቶ ጌታቸው የገንዘብ ቅጣቱ ቀርቶላቸው በሰባት ዓመታት እስራት፣ ዶ/ር መሐሪም በአምስት ዓመታት እስራት እንዲቀጡና የገንዘብ ቅጣቱ እንዲቀርላቸው ተወስኗል፡፡ ሦስቱም ፍርደኞች ለስድስት ዓመታት በእስር በመቆየታቸው በአመክሮ መፈታታቸው ታውቋል፡፡ ዶ/ር መሐሪ ቀደም ሲል የተፈቱ ሲሆን፣ አቶ አያሌውና አቶ ጌታቸው ግን ባለፈው ዓርብ ተፈተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...