Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተጨማሪ አምስት ቢሊዮን ብር ጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተጨማሪ አምስት ቢሊዮን ብር ጠየቀ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተጨማሪ አምስት ቢሊዮን ብር እንዲለቅለት ጠየቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2008 ዓ.ም. ለሚያካሂዳቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አሥር ቢሊዮን ብር በጀት እንዲለቀቅለት የተስማማ ቢሆንም፣ ይህ በጀት የማይበቃው በመሆኑ ተጨማሪ አምስት ቢሊዮን ብር በሚቀጥሉት አምስት ወራት እንዲለቀቅለት ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጨማሪ በጀት ጥያቄ በባንኩ ማኔጅመንት እየታየ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ከአሥር ቢሊዮን ብር ውስጥ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ስድስት ቢሊዮን ብር ተጠቅመዋል፡፡ ከዚያ በኋላ እስካሁን በአጠቃላይ 7.7 ቢሊዮን ብር ተለቆላቸዋል፤›› በማለት አቶ ኤፍሬም ገልጸው፣ ‹‹የአዲስ አበባ አስተዳደር አሁን ተጨማሪ የጠየቀው አምስት ቢሊዮን ብር በባንኩ ማኔጅመንት እየታየ ነው፤›› በማለት አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል፡፡

አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በ2008 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት ከተለቀቀለት በጀት ውስጥ 2.2 ቢሊዮን ብር ለ40/60፣ እንዲሁም 3.8 ቢሊዮን ብር ለ20/80 ቤቶች ፕሮግራም ማዋሉ ታውቋል፡፡

አስተዳደሩ የተፈቀደለትን በጀት ወስዶ ያልጨረሰ ቢሆንም፣ በተጨማሪ እንዲለቀቅለት ከጠየቀው አምስት ቢሊዮን ብር ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ብር ለ40/60፣ የተቀረው ሦስት ቢሊዮን ብር ደግሞ ለ20/80 ቤቶች ፕሮግራም እንደሚውል ከአስተዳደሩ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ 50 ሺሕ የ20/80 ቤቶችን የመገንባት ዕቅድ አውጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የ2008 ዓ.ም. ዕቅድን በሚመለከት  ያቀረቡት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመሩ 39 ሺሕ ቤቶች የግንባታ አፈጻጸማቸው 85 በመቶ ደርሷል፡፡ በቅርቡ ከንቲባው በሰጡት መግለጫ የእነዚህ ቤቶች ግንባታ አፈጻጸም ከ90 በመቶ በላይ በመድረሱ በቅርቡ በዕጣ ይተላለፋሉ ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በ2006 ዓ.ም. የተጀመሩ 50 ሺሕ ቤቶች በአሁኑ ወቅት ግንባታቸው በመገባደድ ላይ ይገኛል፡፡ የ40/60 1,292 ቤቶች የመሠረተ ልማት ግንባታ እየተካሄደባቸው ሲሆን፣ በ2006 ዓ.ም. የተጀመሩ 12,921 ቤቶች ግንባታም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2007 ዓ.ም. የተጀመሩት 12,190 ቤቶችም በመገንባት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ በቤቶቹ ግንባታ ሒደት ጎልተው ከሚነሱ ችግሮች መካከል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና ወቅቱን የጠበቀ የገንዘብ ፍሰት አለመኖር ናቸው፡፡

በተለያዩ መድረኮች እነዚህ ችግሮች ጎልተው የሚነሱ ሲሆን፣ የገንዘብ ፍሰትን በተመለከተ አቶ ኤፍሬም ሲመልሱ፣ የቤቶች ልማት መንግሥት ፋይናንስ እንዲያገኙ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡ ባንኩ ከአስተዳደሩ ጋር በተስማማው መሠረት ፋይናንስ ሲለቅ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ ሥራዎቹን አስፍቶ በሚያካሂድበት ጊዜ ከተጨማሪ ፍላጎት የሚመጣ ክፍተት ሊሆን እንደሚችል አክለዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...