Saturday, September 24, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርት​ስድስት አሠልጣኞች የካፍ ኢንስትራክተር ሆኑ

  ​ስድስት አሠልጣኞች የካፍ ኢንስትራክተር ሆኑ

  ቀን:

  የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የስድስት ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ አሠልጣኞችን የኢንስትራክተርነት ደረጃ ማፅደቁን አስታወቀ።

  የኢንስትራክተርነት ደረጃን ካገኙት አሠልጣኞች አንዱ ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት ቆይታ በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ያበቁት አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ናቸው፡፡

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መረጃ እንዳስታወቀው አብርሃም መብራህቱ፣ አብርሃም ተክለሃይማኖት፣ አንተነህ እሸቴ፣ መኮንን ኩሩና ዶክተር ጌታቸው አበበ በአዲሱ የካፍ ኢንስትራክተሮች አፅዳቂ አካል የኢንስትራክተርነት ማዕረግ ፀድቆላቸዋል፡፡

  የኢንስትራክተርነት ደረጃው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2018 ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡

  ሌሎች በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥር የሚገኙ ኢንስትራክተሮች በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ኃላፊነት አማካይነት የትምህርትና ሥልጠና ዝግጅታቸው እየተገመገመ በአገር ውስጥ እውቅና እንደሚሰጣቸውም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

  ከመጀመርያዎቹ ኢትዮጵያውያን የካፍ ኢንስትራክተሮች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱትና በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ሥልጠና የሰጡት፣ ሰባት ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫዎች የተጫወቱትና በ1974 ዓ.ም. ለ13ኛው የሊቢያው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እንድታልፍ ያደረጉት በኩር (ዘ ሌጀንድ) መንግሥቱ ወርቁ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

  ለቻይናው ፖሊጂሲኤል ኩባንያ የተሰጠው ውል ተቋረጠ

  የማዕድንና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት...

  የሕግ ክልከላዎችና የሚያስነሱት ቅሬታ

  በኢትዮጵያ የአገርና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተብለው የሚወጡ አንዳንድ ሕጎች፣...