ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የጥፋት ኃይሎች አገሪቱን ከመጉዳታቸው በፊት መንግሥት የማያዳግም ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በገለፁበት አጋጣሚ የተናገሩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰንበቻውን በምዕራብ አርሲና በተወሰኑ የሐረር አካባቢዎች እየተፈጠሩ ያሉ ሁከቶች በሒደት መልካቸውን መቀየራቸውን አስታውቀዋል። አያይዘውም በአሁኑ ወቅት ግን ሕዝቡም ጉዳዩን በሚገባ እየተገነዘበ በመሆኑና እነዚህ የጥፋት ኃይሎች ሥርዓቱን የማፈራረስ፣ በነውጥና በሁከት መንግሥትን የመቀየር ተልዕኮ ያላቸው ቡድኖች እንደሆኑ ተረድቷልም ብለዋል፡፡