Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመንግሥትና ለምዕመናን የሰላም ጥሪ አቀረበ

​የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመንግሥትና ለምዕመናን የሰላም ጥሪ አቀረበ

ቀን:

‹‹ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ማክሰኞ የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱት ተቃውሞችና አለመረጋጋቶች አስመልክቶ ባወጣው የአቋም መግለጫና ሃይማኖታዊ ጥሪ፣ መንግሥትንና ምዕመንናን ለሰላማዊ መድረክ እንዲተጉ ጥሪ አቀረበ፡፡

የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት ተጠሪዎች፣ የጉባዔው የቦርድ አባላትና የበላይ ጠባቂዎች በተሰየሙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ኡመር አሚንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል፣ በአገሪቱ እየታየ ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሥጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል፡፡

ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በኦሮሚያ፣ በአማራና በጋምቤላ ክልሎች የተቀሰቀሱና አሁንም ያልበረዱ ግጭቶች አገሪቱን ወደ ኋላ የሚመልሱና እየታየ ያለውን ለውጥ የሚያጠለሹ እንደሆነ በመጠቆም፣ መንግሥትና ሕዝብ ለሰላማዊ መድረክ ትኩረት እንዲሰጡና አለመግባባትን በማርገብ ለዘለቄታዊ መፍትሔ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በግጭቶቹ ምክንያት የሚጠፋው የሰው ክቡር ሕይወት፣ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት ያሳዝናል በማለት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ፣  ‹‹ለዘመናት የተመሰከረልን አብሮ የመኖርና የሃይማኖት መቻቻልን ጥላሸት የሚቀቡ አጋጣሚዎችን በመጥቀስ፣ ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል፤›› በማለት ማንኛውንም ግጭትና አለመግባባት ለመፍታት ውጤታማ የሆነውና ባህላዊው የሽምግልና ሥርዓት መዳከም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በምዕራብ አርሲ በቅርቡ በተፈጠረው ግጭት የሞቱትን ወገኖችና የወደሙ የልማት ተቋማትና መሠረት ልማቶችን በመጥቀስ በጥፋተኝነት የሚወነጀሉ አካላት ሁሉ ለፍርድ መቅረብ እንደሚገባቸው ያሳወቀው የሃይማኖት ተቋማቱ ጉባዔ፣ በቀጣይ መንግሥትና ምዕመናኑ ለሰላም የሚተጉበት ጊዜ እንዲሆን በሁሉም ቤተ እምነቶች ጾምና ጸሎቱ እንዲጠናከርም ጥሪ አድርገዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት በእምነት ተቋማት ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት መቆም እንዳለበት፣ ምዕመናን በየቤተ እምነታቻው የፈጣሪያቸውን ምሕረት በመለመን ለአገርና ለወገን ሰላምን፣ ፍቅርንና መቻቻልን እንዲያበዛ በጸሎት መትጋት እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከስድስት ዓመታት በፊት በሰባት የእምነት ተቋማት መሪዎች የተመሠረተ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡ ተቋሙ በአገሪቱ ለረዥም ዓመታት ፀንቶ  የቆየውን መቻቻልንና ሰላምን በማጠናከር፣ ለሕዝብ አንድነትና ለአገር ብልፅግና የሚሠራ መሆኑን የሃይማኖት መሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...