Monday, October 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረት​የአፍሪካ የዱር ውሻ

  ​የአፍሪካ የዱር ውሻ

  ቀን:

  የአፍሪካ የዱር ውሾች በጥበበኛ የተነደፈ በሚመስለው የፀጉራቸው ቀለም አጣጣል ይለያሉ፡፡ ነጭ፣ ጥቁር፣ ቡናማ፣ ወርቃማና ቢጫ ፀጉር ሲኖራቸው፣ የቀለሙ አጣጣልም የአንዱ ከሌላው ጋር አይመሳሰልም፡፡ ሠፋፊ ጆሮ፣ ረዥምና ፀጉራም ጭራ እንዲሁም ረዣዥም እግር አላቸው፡፡ ጣቶቻቸውም እንደሌሎች ውሾች አምስት ሳይሆኑ አራት ናቸው፡፡

  በደቡብ አፍሪካና በምሥራቅ አፍሪካ በብዛት የሚገኙት የዱር ውሾች በአዳኝነታቸው ይታወቃሉ፡፡ ለማደን ካለሙት እንስሳ 80 በመቶ ያህሉን ይይዛሉ፡፡ ይህ ከአንበሳ ጋር ሲነፃፀር በ50 በመቶ ያህል ብልጫ አለው፡፡

  ኑሮዋቸው በቡድን ሲሆን፣ በአንድ ቡድን ውስጥ ከ10 እስከ 40 ውሾች አብረው ይኖራሉ፡፡ በአዳኝነታው የሚታወቁት የዱር ውሾች፣ በሰዓት እስከ 44 ማይልስ ድረስ የሚሮጡ ሲሆን፣ ጉልበታቸው (ኃይላቸው) ካላቸው የሰውነት ክብደት ጋር ሲነፃፀር በዓለም ከሚገኙ እንስሳት ይበልጣል፡፡

  የመኖር ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 12 ዓመት ነው፡፡ አንድ ውሻም በአንዴ ከሁለት እስከ 20 ቡችሎች ትወልዳለች፡፡

  እነዚህ ዝርያዎች ከደን ምንጣሮና ከሕዝብ አሰፋፈር ጋር ተያይዞ እየተመናመኑ ነው፡፡ በአንድ ወቅት እስከ 500 ሺሕ ይደርሱ እንደነበር፣ አሁን ላይ ግን ከ3 ሺሕ እስከ 5 ሺሕ እንደሚሆኑ ዳክስታር በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img