Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹ጀግኖች አልፈዋል …››

‹‹ጀግኖች አልፈዋል …››

ቀን:

ከሰባ ዘጠኝ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የፋሺስት ኢጣሊያ ጭፍራዎች ከየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. አንስቶ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ባደረጉት ፍጅት 30 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ የሰማዕታቱ መታሰቢያ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ሐውልታቸው የካቲት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ታስቦ ውሏል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከተገኙት አንዱ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳነት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን (ከቀኝ 4ኛው) ‹‹ጀግኖች አልፈዋል፤ ታሪካቸው፣ አልነካባይነታቸውና ልዕልናቸው ግን አያልፍም፤›› ብለዋል፡፡

​*********

ወይ ታሪክ!

ታሪክ እነፍሴ ዲብ እየሠራ

ዘመን እልቤ ከምሮ ጋራ

ቀና ቀና ስል ምንም ሳልፈራ

ክብረ ቢስ ችግር ክብሬን ገሶ

ተልኮሰኮስኩኝ ኩራቴ ኮሶ

በልቶ ለማደር አጎነበስኩኝ

ለፍርፋሪ ሞገሴን ሸጥኩኝ፡፡

          የአያት ቅድም አያት ያባት እናቴ

          የጀግንነቱ ገድሌ ንግርቴ

          እልፍ እጥፍ ነበር ዋጋው ግምቱ

          ረከሰና ጉርስ ሆነ የዕለቱ

          ጊዜ አዘንብሎ ተደፍቶ አንገቴ

          ክብሬ ገበያው ሆነ ለእራቴ

ላብን አፍስሰው በአቅም ሳይጥሩ

ጥሪት ሰብስበው ሠርተው ሳይከብሩ

ወይ ታሪክ እቴ ገድል ቢያወሩ

ኮርቶ ለማደር የል ጦም እያደሩ፡፡

  • ተፈሪ ዓለሙ ‹‹የካፊያ ምች›› (2001)

*********

የጋብቻ ሥነ ሥርዓትን በውኃ ገንዳ

ደስቲንና ክሪስታል የተባሉ ጥንዶች ጋብቻቸውን ለባህር እንስሳት መኖሪያነት በሰው ሠራሽ መንገድ በጆርጅያ አትላንታ በተሠራ የውኃ ገንዳ ውስጥ ፈጸሙ፡፡ ዩኤስኤ ቱዴይ እንደዘገበው፣ ጥንዶቹ ወንዱም ቶክሲዶውን ሴቷም የሙሽራ ልብሷን እንደለበሰች ዓሳ፣ ዓሳ ነባሪና ሌሎች የባህር እንስሳት እንዲሁም ቅጠላ ቅጥሎችን በያዘው ዘመናዊ የውኃ ገንዳ ውስጥ ቃለ መኃላ ፈጽመዋል፡፡ ሙሽራው ‹‹የባህር እንስሳት በሚኖሩበት የውኃ ገንዳ ውስጥ ጋብቻችንን እንፈጽማለን ብለን አስበን አናውቅም፡፡ ሆኖም ሁለታችንም ለመዋኘት ያለን ፍቅር፣ የምንመኘውን ነገር በምንወደው ሥፍራ እንድናደርግ አድርጎናል፤›› ማለቱን ዘገባው ያሳያል፡፡

ሙሽሮቹ የመጀመርያ ዳንሳቸውን ከደነሱ በኋላ በውኃ ገንዳው (አኳርየም) ውስጥ በሚገኘው ቦልሩም የሪሰፕሽን ግብዣ አድርገዋል፡፡ የውኃ ገንዳው 3.6 ሚሊዮን ጋሎን ውኃ የያዘ ነው፡፡

********

ኣልም

በመሆን ጎዳና ላይ ቀዳሚው ዕርምጃ ማለም፣ የነፃች ህልም ማለት ነው፡፡ ይህ ጉዞህን ለመጀመር ኣክናፍ፣ ለመጨረስም የፅናት ሰቅ ይሰጥሃል፡፡

የበቁ ተጓዦች፣ ዕይታህን ከውጤት ላይ አንሳና መንገድህ ላይ አድርግ፤ ይላሉ፡፡ የሚያድንህ መንገዱ እንጂ ውጤቱ አይደለምና፡፡

መንገድህ በዚያ ያለው እንድትራመደው ነው፡፡ ተጓዘውና እመድረሻህ ላይ ምን እንዳለ ተመልከት – የዕርምጃህ ንፅህና በሚገልጽልህ መድረሻ ላይ ምን እንዳለ፣ የሌላ ህልም መጀመርያ እንጂ ሌላ ባይደለው መድረሻ ላይ ምን እንዳለ፣ ጉዞህን ተጓዝና እይ፡፡

እመጀመሪያይቱ ላይ ሆነው የመጨረሻይቱን ማለም ከሚመርጡቱ፣ ወይም ማለም እንችላለን ከሚሉቱ፣ ባለዕቅዶች ወገን ነህ? ከሆነ፣ መልካም ነው፡፡ ግና፣ ግብህን አክናፍህን ሊተበትብ ከሚችል ነገር ሁሉ አንፃው፡፡

ሕይወት ራሷ አቧራማ መንገድ ነች፡፡ በጉዞህ መጀመርያ ላይ መንፈስህ ነፅቶ መቆሸሽን እምቢኝ ካላላ በቀር፣ ያለጥርጥር፣ በውስጥህ ያለው ጉድፍ ከምታኖራት ከእያንዳንዷ ዕርምጃ ጥቀርሻ እየጠቀሰ ገዳይነቱን ያበዛል፡፡ አንፃው፡፡ በሰም ወልውለህ ፍፁም አንፃው፡፡

ይህ ግልጽ ጥበብ ነው፡- እርጥብ እንጨት እምድጃህ ሞጅረህ በጭሱ እያነባህ በስቃይ ከምትኖር፣ እንጨትህን አሳምረህ አድርቀው፡፡

  • ኦ’ታሞ ፑልቶ (2006)

**********

ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ የሌለባቸው ምግቦች

ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆዩ በማሰብ ምግቦችን በሙሉ ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ የብዙዎች ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ ምግቦች ፍሪጅ ውስጥ መቀመጣቸው ከመቆየት ይልቅ ወዲያው እንዲበላሹ፣ ጣዕምና ይዘታቸው እንዲቀየር እንደሚያደርግ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የዘ ኢንዲፔንደንት ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ቲማቲም ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ ከሌለባቸው ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ቲማቲም ፍሪጅ ውስጥ ሲገባ መብሰሉን ያቆማል፣ ጣዕሙንም ያጣል፡፡ ይህ የሚሆነው ፍሪጅ ውስጥ መግባቱ የኬሚካል ይዘቱን በመለወጥ ፍሬው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው ድንች፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩር፣ ዳቦና ሙዝ ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ ስለሌለባቸው  ምግቦች ናቸው፡፡

********

ብራዚላዊው ለመዝናናት ሲል 41 ሰዎችን መግደሉን አመነ

በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ ከከተማ ወጣ ባለ አካባቢ አንዲት ሴትን በስለት በመውጋት የተጠረጠረው ሰው፣ ቀደም ሲልም 41 ሰዎችን ለመዝናናት ሲል መግደሉን እንዳመነ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ግለሰቡ ከገደላቸው መካከል ከሞላ ጎደል ብዙዎቹ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ወንጀለኛው እየተከታተለ መውጫ መግቢያቸውን አጥንቶ በስለት በመውጋት የሚገድላቸው ነጭ ሴቶች ናቸው፡፡ የአዕምሮ ችግር እንዳለበት የተጠረጠረው የ26 ዓመቱ ሴልሰን ጆዝ ዳስ ግራሳስ 37 ሴቶችን፣ ሦስት ወንዶችንና አንድ ሕፃን ልጅን በዘጠኝ ዓመት ውስጥ ገድሏል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...