Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህል​የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን የሚገልጠው መዘክር

​የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን የሚገልጠው መዘክር

ቀን:

በኢትዮጵያ ‹‹ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች›› ይኖራሉ እየተባለ በተለይ ከሩብ ምእት ዓመት ወዲህ ከመንግሥት ለውጥ በኋላ ሲነገር ይሰማል፡፡ በአገሪቱ ያሉት ብሔረሰቦች ቁጥር በርግጥ ስንት ነው የሚለውን ለመወሰን በተለይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዴሚና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ከተነገረ ቆይቷል፡፡

የ1966ቱን የኢትዮጵያ አብዮት ተከትሎ የተመሠረተው የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ብሔረሰቦችን በተመለከተ ካከናወናቸው ተግባራት አንዱ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ኢንስቲትዩትን መመሥረቱና የተለያዩ ጥናቶች ማድረጉ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን (ኢሠፓአኮ) /1972 – 1976/ በቀጣይነትም በኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) /1977 – 1983/ ሥር የብሔረሰቦች ጉዳይን በሚመለከተው መምርያ ሥር ይመራ የነበረው ኢንስቲትዩቱ ብሔረሰቦች ብዛታቸውን፣ ዓይነታቸውንና አሰፋፈራቸውን አጥንቶ መሰነዱና ለሚመለከተው አካል ማቅረቡ ይታወቃል፡፡

በዘመኑ ለአንባብያን ያልቀረበው የጥናት ውጤት መሰንበቻውን በወቅቱ ከነበሩት የዩኒቨርሲቲ ምሁራን አጥኚዎች መካከል አንዱ ዶ/ር ፍሥሐ አስፋው ‹‹የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን የሚገልጥ ጥናታዊ መዘክር – ብዛት፣ ምንነት፣ ማንነትና አሰፋፈር›› በሚል ርእስ አሳትመው ለአንባቢያን አድርሰዋል፡፡

- Advertisement -

ዶ/ር ፍሥሐ በመግቢያቸው ላይ እንደገለጹት፣ የዚህ ‹‹የብሔረሰቦች ማወቂያ›› በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ ለሕዝብ እንዲደርስ የተደረገበት ዓላማው የአሁኑ ትውልድ ስለ ኢትዮጵያ ብሔረሰቦች የሚያነበውና የሚሰማው ግለሰቦች ወይም የተወሰኑ ቡድኖች ከራሳቸው የግል አመለካከትና ከሚያገኙት የፖለቲካ ተረፌታ በመነሳት ከሚጽፉትና ከሚናገሩት ስለሆነ ይሄን በሐቅና በጥንቃቄ የተጠና የመስክ ጥናት በመመልከት ሙሉና እውነተኛ መረጃ በማግኘት ስለ ሀገሩ ሕዝቦች እውነቱን እንዲያውቅ ለማድረግ ነው፡፡

በተጨማሪም ለመጪውም ትውልድ የታሪክ መዛግብት እንዲሆንና ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል ምን ዓይነት ኢትዮጵያዊ እንደሆነና ታሪኩም ሆነ ባህሉም በአንድ፣ በሁለት ወይም በሦስት ብሔረሰቦች ብቻ የተገነባ አለመሆኑን እንዲያውቅ ለማድረግም መጻፉን አዘጋጁ ገልጸዋል፡፡

መጽሐፉ የኢትዮጵያን ብሔረሰቦች ሥርጭት በጥቅል መልኩ በአገር አቀፍ ደረጃ በሦስት ረድፎች ከፍሎታል፡፡

አንደኛው ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላቸው፣ ሰፋፊ አካባቢ የያዙ፣ በኢኮኖሚ የዳበሩና በተመጣጣኝ የባህል ዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ባለው ደጋማ መሀል አገር የሚኖሩ ብሔረሰቦችን አማክሏል፡፡

ሁለተኛው እነዚህን ባለብዙ ሕዝብ ብሔረሰቦች እያጐራበቱና እያዋሰኑ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ እንደዚሁም በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ ጠረፎች ዙሪያ የሚኖሩ፣ በኢኮኖሚ ኋላቀር የሆኑ ገና በዝቅተኛ የባህል ዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ፣ የሕዝባቸው ብዛት ከጥቂቶች በቀር በጣም አነስተኛ የሆነ አናሳ ብሔረሰቦች ያላቸው ብሔረሰቦች እንደሚኖሩ አመላክቷል፡፡

ሦስተኛው በኢኮኖሚና በባህል ዕድገታቸው ከእነዚህ በአንደኛው ረድፍ ከተጠቀሱት ብሔረሰቦች የሚነጻጸሩ፣ ብዙዎቹ መለስተኛ የሕዝብ ብዛት ያላቸው በመጀመሪያዎቹ ብሔረሰቦች በከፊል በመከበብ፣ ወይም በሙሉ በመታቀፍ፣ በአንዳንድ አካባቢ ደግሞ በጠረፍና በመሀል ሀገር በሰፈሩት ብሔረሰቦች መካከል የሚገኙ ብሔረሰቦች እንዳሉ ጠቅሷል፡፡

ከ574 ወረዳዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን በያዘው መጽሐፍ የመጀመሪያ ክፍል የ75 ብሔረሰቦች ምንነት፣ ማንነትና አሰፋፈር በአጭሩ ተገልጽዋል፡፡ በአባሪነት በሰፈረው የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ስም ዝርዝር መግቢያ ላይ ኢንስቲትዩቱ ካሰባሰበው መረጃዎች አንፃር የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ዝርዝር 89 ይደርሳል፡፡ ይሁን እንጂ አኀዙ የመጨረሻ እንደማይሆንና ቁጥሩ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ የሁሉም ብሔረሰቦች የስም ዝርዝር የተጻፈ ሲሆን፣ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራና ትግራይን ‹‹ትግራይ ትግርኝ›› በሚል አስቀምጦታል፡፡

የብሔረሰቦቹ ቁጥር ይፋ አኃዝ ሳያገኝ በመውጣትና በመውረድ ላይ መገኘቱ  የተለያዩ ምክንያቶች ሲኖሩ ዋናው የብሔረሰቦች ስያሜ አለመጣራት ነው፡፡ ከጥቂት ብሔረሰቦች በቀር ሁሉም ብሔረሰቦች እያንዳንዳቸው አያሌ መጠሪያ አላቸው፡፡ አንድ ብሔረሰብ ራሱ የሚቀበለውና የሚያምንበት አንድ ስም ሲኖረው ሌሎች የሰጡት ስያሜ አለው፡፡ የቋንቋና የስነ ሰብ ምሁራን ያወጡለት ሌላ መጠሪያ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም እንደዚህ ያለው ድርብርብ ስምና መጠሪያ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን ቁጥር ሊያበዛው ችሏል፡፡ አንዳንድ ብሔረሰብ በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ ተመሳሳይ ሲሆኑ በስያሜ ይለያያሉ ይላል ጥናታዊው ድርሳን፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...