Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትካለፈው የቀጠለ መልካም ጅምር

  ካለፈው የቀጠለ መልካም ጅምር

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ስፖርትን በትናንት ታሪኩ ከተመለከትነው በተለያዩ ክፍተቶች የመጠመዱን ያህል ዘለቄታዊ ውጤትን ግብ ያደረገ አስተዳደራዊ መርሆች እንደነበሩት መመልከት ይቻላል፡፡

  ባለፉት ሥርዓቶች ጠንካራ እንደነበርም የሚነገርለት የትምህርት ቤቶችና የወረዳዎች ስፖርታዊ ፉክክሮች በጥሩ በጀትና በጥሩ አመለካከት እንዲሁም በፍትሐዊ የበጀት ድልድል በመመራቱ ጭምር እንደነበር የሚናገሩ አሉ፡፡ አሁን የሚታየውን የተዳከመ የትምህርት ቤቶችና የወረዳዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ለማጎልበት ሁነኛው መፍትሔም ለስፖርቱ መሠረት የሆነውን የበጀት አመዳደብና አቀማመጥ እንዲሁም አስተዳደራዊ መዋቅሩ እንደሆነም የሚያምኑ አሉ፡፡

  በቅርቡ በአዲስ የተዋቀረው የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በዚህ የበጀት አቀማመጥና አወቃቀር ሑደት ላይ እንዲሁም የትምህርት ቤቶችና ፕሮጀክቶች ሥልጠናን መነሻ በማድረግ እያሳየ የመጣው መልካም ጅማሮ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን የሚመሰክሩ አሉ፡፡

  ሚኒስቴር ከየካቲት 15 እስከ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በአዳማ ሪፍቲ ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባዘጋጀው የትምህርት ቤቶችና ፕሮጀክቶች የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ ከፊል ኦሮሚያ ከፊል ደቡብና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ 675 ሠልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡ የዚህ ተመሳሳይ ሥልጠና ድሬዳዋ ከተማ ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር ከሐረርና ከኢትዮጵያ ሱማሌ የተውጣጡ ሠልጣኞች፣ ባህር ዳር ከተማ ላይ ደግሞ ከመጋቢት 21 እስከ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ የአማራ፣ የትግራይና የአፋር ሠልጣኞች እንዲሁም ጅማ ከተማ ላይ ከፊል ኦሮሚያና ከፊል ደቡብ፣ የቤንሻንጉልና የጋምቤላ የትምህርት ቤቶችና የፕሮጀክት አሠልጣኞች ሥልጠና እንደሚቀጥል በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሲሳይ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡

  እንደ አቶ ሲሳይ፣ ሚኒስቴሩ ከዚህ የትምህርት ቤቶችና ፕሮጀክቶች አሠልጣኞች ሥልጠና ጎን ለጎን ያለፈው አምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የነበረውን ጠንካራና ደካማ ጎን ከገመገመ በኋላ በቀጣዩ አምስት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ይኖር ዘንድ በመነሻነት የወሰደና ያለመ ነው፡፡

  ከሥልጠና ማንዋል ዝግጅት እስከ ማዘውተሪያ ስፍራ እንዲሁም እንዳለፉት ዓመታት ዓይነት በሪፖርት የበለፀገ የዕቅድ አፈጻጸም ከእንግዲህ ቦታ እንደሌለው ያስረዱት ኃላፊው፣ ይህ አሁን የተጀመረው የትምህርት ቤቶችና ፕሮጀክቶች አሠልጣኞች ሥልጠና ከሚኒስቴሩ ጀምሮ ትምህርት ሚኒስቴር፣ አገር አቀፉ የስፖርት ማኅበራት፣ ክልሎችና ሌሎች የማመለከታቸው ሁሉ እያንዳንዱ የራሱ የሆነ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ ወስዶ ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥር መረከብ የሚያስችል የሥራ ድርሻ ኖሮት ክትትልና ቁጥጥሩም በዚያው ልክ ተፈጻሚ እንደሚሆን በመንግሥት ግልፅ አቅጣጫ የተቀመጠለት መሆኑን ጭምር ተናግረዋል፡፡

  እስከዛሬ በነበረው አሠራር ታች መሠረቱ ላይ የበጀትና ቁሳቁስ አቅርቦት ውስንነት ተንሰራፍቶ መቆየቱ ለስፖርቱ መዳከም የጎላ ድርሻ ሲያበረክት መቆየቱ፣ የማዘውተሪያ ስፍራ እጦት፣ ከፍተኛ የአፈጻጸምና የአስፈጻሚ አካላት ክፍተቶችና ሌሎችም ችግሮች ሚኒስቴሩ አሁን ባቀደው ሁኔታ መፍትሔ ለማግኘታቸው ጥርጣሬ እንዳላቸው የሥልጠናው ተሳታፊዎች ያለምንም ገደብ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡

  ካለፈው አምስት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመነሳት በተሳታፊዎቹ የሚነሱት ክፍተቶችና ድክመቶች የጠንካራ ጎኑን ያህል እንደነበሩ ያስታወሱት ተወካዩ፣ ለወደፊቱ ግን የነበረው እንደማይቀጥል ከታች ከትምህርት ቤቶችና ፕሮጀክት ጀምሮ እስከ አስፈጻሚው አካል የየራሱ የኃላፊነትና የሥራ ድርሻ ወስዶ ተጠያቂነቱም በዚያው መጠን ተግባራዊ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

  ከታች ከሕፃናት ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ15፣ 17 እና ከዚህም በላይ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችና ፕሮጀክቶች ከጊዜው ጋር መሄድ የሚችሉ ማሠልጠኛ ማንዋሎች በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርና ከአገር አቀፍ የስፖርት ምክር ቤት በተውጣጡ ባለሙያተኞች ተዘጋጅቶ ለእያንዳንዱ የትምህርት ቤትና ፕሮጀክቶች አሠልጣኞች እንደሚሰጥም ተወካዩ አቶ ሲሳይ ተናግረዋል፡፡ ተግባራዊነቱን በተመለከተ የአገሪቱ የስፖርት ሚዲያ ቦታው ድረስ በመሄድ ትክክለኛውንና መሬት ላይ ያለውን በመዘገብ ለመንግሥትና ለኅብረተሰቡ የማድረስ ኃላፊነት እንዳለበት ጭምር ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአገሪቱ በ17 የስፖርት ዓይነቶች ወደ 50,000 የሚጠጉ ታዳጊ ወጣቶች በሥልጠናው እንደሚካተቱም ተመልክቷል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...