Sunday, April 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አቢሲንያ ባንክን ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ የሚገኘው የኢቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ በስለት በማስፈራራት ዘረፋ ለመፈጸም የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡

ሪፖርተር በቅርንጫፍ ባንኩ ተገኝቶ ከዓይን እማኞችና ከመርማሪ ፖሊሶች ለመረዳት እንደቻለው፣ ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ባንኩ የገቡ ዘራፊዎች በስለት በማስፈራራት በባለ 50 ኪሎ ግራም ሁለት የማዳበሪያ ከረጢቶች አንደኛው ውስጥ ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ በማጨቅ ዘርፈው ለመወሰር ሙከራ ቢያደርጉም፣ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ርብርብና በትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ ሊያዙ መቻላቸው ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ 5.58 ሚሊዮን ብር ከባንኩ ለመዝረፍ መሞከራቸው ታውቋል፡፡ 

የዓይን እማኞች ለሪፖርተር እንደተናገሩት ከሆነ፣ ተጠርጣሪዎቹ 5.58 ሚሊዮን ብር በሁለቱ ከረጢቶች ሞልተው አንደኛውን በቪትዝ መኪና ጭነው ለመጓዝ ሲሞክሩ ተይዘዋል፡፡ በማዳበሪያ ከረጢት የያዙትን ገንዘብ ጭነው ሲጓዙ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በነበረው የትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ ከሁለት መኪኖች ጋር ሲጋጩ፣ በሥፍራው በነበረ ማስቲካ አዟሪ ጠቋሚነት በፖሊስ ቁጥጥር መዋላቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡

የቦሌ ካራማራ ፖሊስ ወንጀሉ የተፈጸመበትን የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ ጥበቃዎችን ጨምሮ የቅርንጫፉን ኃላፊዎችና ሌሎችም ሠራተኞች በመርመር ላይ እንደሚገኝ በማስታወቅ፣ ስለወንጀሉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ የአቢሲንያ ባንክ ፕሬዚዳንትና ሌሎች ኃላፊዎች ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

ከባንኩ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ለመረዳት እንደተቻለው ግን በፖሊስ ጣቢያ በኤግዚቢትነት ተይዞ የነበረው ገንዘብ ተመላሽ መደረጉን፣ ፖሊስ ባለበት በተደረገው ቆጠራ አንዳችም ገንዘብ እንዳልጠፋም ተረጋግጧል፡፡ በቆጠራው ወቅት ሊዘረፍ የነበረው ገንዘብ 5.58 ሚሊዮን ብር እንደነበር ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች