Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናኢሃን መንግሥት ታሪክ ይቅር የማይለው አገራዊ ክህደት ፈጽሟል አለ

  ኢሃን መንግሥት ታሪክ ይቅር የማይለው አገራዊ ክህደት ፈጽሟል አለ

  ቀን:

  በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በነበሩት ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) የሚመራው የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን)፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ታሪክ ይቅር የማይለው አገራዊ ክህደት መፈጸሙን አስታወቀ፡፡

  ኢሃን ሰኔ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያውያን ለተከታታይ ትወልዶች በከፈሉት መስዋዕትነት ሉዓላዊነቷንና ነፃነቷን አስከብራ የኖረች አገር ነበረች፡፡ ይኼንን የትውልዶች ብሔራዊ ክብር በመናድ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ፣ ሁለት ዋነኛ ጉዳዮች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ታሪክ ይቅር የማይለው አገራዊ ክህደት መሆኑን አስታውቋል፡፡

  የፓርቲው ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) እንደሚያስረዱት፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ሁለት አንኳር ታሪካዊ ስህተቶች ፈጽሟል፡፡ አንደኛው ከሰባ ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን የተሰውለትን ባድመን የዳር ድንበር ክብር ባልተጠበቀና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አሳልፎ መስጠቱን ነው፡፡ ሌላው ሁለተኛው ስህተት ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ተብሎ በአፍሪካ መሪና በዓለም ተወዳዳሪ የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለሽያጭ ማቅረቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  መንግሥት ባልተጠና ፖሊሲ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ብሎ፣ የአገሪቱን ጥሪት አሟጦና ያለባትንም ብሔራዊ ዕዳ ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር በማሳደግ ለሙስና መንገድ መክፈቻ የጀመራቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች እንደተጀመሩ ሜዳ ላይ መቅረታቸውንም ገልጸዋል፡፡ በሜዳ ላይ የቀሩ ፕሮጀክቶች በአገር ላይ ያደረሱት የኢኮኖሚ ቀውስ ሳይበቃው፣ የአገር ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለሽያጭ ማቅረብ ተገቢ እንዳልሆነም አክለዋል፡፡

  ሁለቱ ውሳኔዎች የአገርና የሕዝብን ጥቅም አሳልፈው የሰጡ የክህደት ውሳኔዎች መሆናቸውን እንደሚያምኑ የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ በመንግሥት የውሳኔ ሰጪ አካላት የተላለፉ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

  ሕዝቡም ከትውልድ ተጠያቂነት ለመዳን ውሳኔውን በማውገዝ፣ ውሳኔው እንዲቀለበስ በጋራ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ኢትዮጵያን እንደ አገርና ሥርዓቱንም ሕገ መንግሥታዊ አድርገው የሚቆጥሩ ውሳኔውን ከማራገብ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደገለጹት፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንድታደርግ፣ ግዙፍ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ፣ እንዲሁም መንግሥት ከፍተኛውን ድርሻ ወስዶ የተወሰኑትን ለሽያጭ እንዲቀርቡ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው፡፡   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...